በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወለጋ ህፃናት በምግብ እጥረት እየሞቱ ነው


በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀሙሩ ጉዪ ቴቦ ቀበሌ የሰፈሩ ተፈናቃዮች "ላለፉት ሶስት ወራት የእህል ድጋፍ በመቋረጡ ከ10 በላይ ሕፃናት በምግብ እጥረት ሞቱ" ሲሉ ገለፁ፡፡

የወረዳውና ዞኑ አደጋ ሥጋት አመራር ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች ድጋፉ የተቋረጠው ለሦስት ወር ሳይሆን ለሁለት ወር ነው ካሉ በኋላ ለበላይ ባለሥልጣን አመልክተው መልስ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፤ ስለ ህፃናት መሞት የሰሙት እንደሌለም ገልፀዋል::

የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በበኩሉ፣ ድጋፉ የዘገየው እህል ለማድርስ በዝናብ ምክንያት መንገድ ስለማያስገባ ዕርዳታው በፍጥነት በገንዘብ መልክ ይሰጣቸዋል ሲሉ አስታውቀዋል::

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በወለጋ ህፃናት በምግብ እጥረት እየሞቱ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:06 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG