በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮምያ ክልል በታጣቂዎች ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ


በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ “ማንነታቸው አልታወቀም” በተባሉ ታጣቂዎች ትናንት ማታ መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

በሌላ በኩል በቄለም ወለጋ ጊዳሚ ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ምሽት ላይ ሁለት ሰዎች “በመንግሥት ታጣቂዎች ተገድለዋል” ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የወረዳው አስተዳዳሪ ሰዎቹ መገደላቸው እውነት እንደሆነ ገልፀው “ቀደም ሲል ግን በመንግሥት ወታደሮች ላይ በታጠቀ ኃይል ቦምብ በመወርወሩ ሰዎቹን የገደለው ማን እንደሆነ አልታወቀም” ብለዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኦሮምያ ክልል በታጣቂዎች ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG