በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ


አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ
አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ

በማህበራዊ መገናኛ ከ420 ሺ ብር በላይ በማሰባሰብ ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን በደብተርና እስክሪብቶ መደገፋቸውን "የነቀምቴ ልጆች" ፌስቡክ ገፅ አስተባባሪ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

"አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ዘመቻ እንዲሳካ በአገር ውስጥና ውጭ አገር የሚገኙ የነቀምቴ ተወላጆችና ሌሎችም መሣተፋቸውን አስተባባሪው ገልፀዋል።

በከተማው ለሚገኙ ችግረኛ ሴት ተማሪዎችም የግል ንፅሕና መጠበቂያዎችን ለማደል እየሠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል::

የከተማዪቱ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ይህ ተግባር በ11 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ችግረኛ ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:45 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG