ዋሺንግተን ዲሲ —
ሰሞኑን በውጥረት ውስጥ በሰነበቱት ሻኪሶና ለገደምቢ ከተሞች ዛሬ የመከላከያ ኃይል አባላት መግባታቸውን ነዋሪዎቻቸው ገልፀዋል። አዶላ ዋዩ ውስጥ ከትናንት በስተያ የተገደለ ጓደኛቸውን አስከሬን ለመቅበር ይሄዱ በነበሩ ባጃጅ ነጅዎች ላይ ድብደባ መፈፀሙም ተሰምቷል።
የሰሞኑ ውጥረት ዛሬ ቢረግብም የወታደሮቹ በከተሞቹ ውስጥ መታየት በሰዉ ስሜት ላይ ጫና ማሳደሩን ነዋሪዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ሰሞኑን ወደ ሻኮሶ ሄደው መነጋገራቸው ተገልጿል።
የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የለገደምቢ ጎልድን ወርቅ የማውጣት ፈቃድ እንደማያራዝም አስታውቋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ