በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊያን ሴናተሮች በአፍሪካ


ክሪስ ኩንስ
ክሪስ ኩንስ

ዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አምስት አባላት ሰሞኑን አራት የአፍሪካ ሃገሮችን በጎበኙበት ወቅት የተደረገላቸው አቀባበል የሞቀ እንደነበርና በትረምፕ አስተዳደር ላይ የተሰሟቸውን ቅሬታዎች የገለፁላቸው እንደነበሩ አመልክተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ዚምባብዌ ላይ ጥላቸው የቆዩ ማዕቀቦችን እንድታነሣ የሚያስችላት መንገድ የሚወስድ የሕግ ረቂቅ ለማቅረብ እየተዘጋጁ መሆናቸውን ሰሞኑን ወደ አራት የአፍሪካ ሃገሮች ተጉዘው የነበሩ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት አስታወቁ።

ሴናተሮቹ በአፍሪካ ሃገሮች ጉብኝታቸው ወቅት የተደረገላቸው አቀባበል የሞቀ እንደነበር ገልፀዋል።

የሴናተሮቹ የሰሞኑ ጉዞ የነበረው ወደ ምዕራባዊ አፍሪካ ሃገሮቹ ቡርኪና ፋሶና ኒዠር፣ እንዲሁም የደቡባዊ አፍሪካ ሃገሮች ዚምባብዌና ደቡብ አፍሪካ ነበሩ።

ዴሞክራቶቹ የዴላወሩ ክሪስ ኩንስ፣ የኒው ጀርሲው ኮሪ ቡከር፣ የኮሎራዶው ማይክል ቤኔትና የሚሺጋኑ ጌሪ ፒተርስ እንዲሁም ሪፐብሊካኑ የአሪዞና ሴናተር ጄፍ ፍሌክ ወደ አፍሪካ የሄዱት የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪካን ግንኙነቶች ለማጠናከር መሆኑን፣ ያሰቡትንም ማሳካታቸውን ገልፀዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም ከፕሬዚዳንቶች እስከ ሲቪክ ማኅበረሰብ መሪዎች፣ ከወጣት እስከ አስተማሪ፣ ከነጋዴ እስከ ወታደራዊ ባለሥልጣናት አግኝተው ማነጋገራቸውን ጠቁመው አፍሪካን በሚመለከት የሁለቱም የዩናይትድ ስቴትስ ገዥ ፓርቲዎች አቋም በሆነ ሁኔታ አብሮ የመሥራት ባሕል ያላት መሆኑን አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አሜሪካዊያን ሴናተሮች በአፍሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:41 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG