በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስለ ሥልጣን ዘመን ገደብ


የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በያዙት ሕዝብን በቀጥታ የማግኘትና የማነጋገር ዘመቻ ገፍተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑንም ወደ ደቡብ ጎራ ብለው ሃዋሣ ላይ ሲናገሩ “ከእንግዲህ በኢትዮጵያ አንድም እስኪገፉ፣ አንድም እስኪያልፉ ሥልጣን ላይ መሟዘዝ አብቅቶለታል” የሚል መልዕክት ያስተላለፈ ብዙውን አድማጭ ንግግራቸውን እንኳ ሳይጨርሱ ያስጨበጨበላቸውን ንግግር አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት የአገልግሎት ጊዜ ቆርጦ የሁለት ዘመናት ገደብ የጣለው ስለወግ ሲባል ባለው የፕሬዚዳንት ቦታ እንጁ የሥራ አስፈፅሚ አቅም ባለው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በሆነው የመንግሥቱ መሪ ላይ አልነበረም።

ለመሆኑ ሕገመንግሥቱ ሲሠራ ይህ ጉዳይ እንዴት ተዘለለ? የሕገመንግሥት ያረቀቀና ያፀደቀውን ጉባዔ በሊቀመንበርነት የመሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ተነጋግረዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስለ ሥልጣን ዘመን ገደብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:07 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG