በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬስ ነፃነት በምሥራቅ አፍሪካ


Reporters Without Borders (RSF) presents the 2018 press freedom barometer.
Reporters Without Borders (RSF) presents the 2018 press freedom barometer.

ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የፕሬስ ነፃነት ይዞታ እያሽቆለቆለ መምጣት በዘንድሮው የፕሬስ ነፃነት ቀን የመብቶች ተሟጋቾች ብዙ ትኩረት የሰጡት ጉዳይ ሆኗል።

ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲና ሶማሊያ የፕሬስ ነፃነት የሌለባቸው ሃገሮች እየተባሉ ወትሮም የሚፈረጁ ሲሆኑ ባለፉ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ግን እንደኬንያና ታንዛንያ ዓይነት ወትሮ የተሻለ ነፃነት እንዳለባቸው የሚነገርላቸውን ሃገሮች ጨምሮ በመላ ምሥራቅ አፍሪካ የሚታየው ሁኔታ እየተበላሸ መምጣቱ ይሰማል።

ድንበር የለሽ ሪፖርተሮች - አር. ኤስ.ኤፍ. የሚባለው የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ቡድን ኢትዮጵያን በፕሬስ ነፃነት ይዞታዋ ከ180 ሃገሮች 150ኛ ቦታ ላይ አስቀምጧታል።

በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ለፕሬስ ነፃነት መጥፋትና ለአፈና እንደሰበብ ተዘውትሮ ከሚነሱ ችግሮች መካከል ሽብር ፈጠራና ብሄራዊ ደኅንነት ዋናዎቹ ናቸው።

የፕሬስ ነፃነት ሲነካና ሲገደብ ዜጎች ሊጨነቁ፣ ሊጮኹ እንደሚገባ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ዳይሬክተር ዶያን ንያንንዩኪ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያንብቡ።

የፕሬስ ነፃነት በምሥራቅ አፍሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:51 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG