በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሚሺን አካምፕሊሽድ!” - ትረምፕ - “የላቀ ሚሳይል እንልካለን” - ፑቲን


የሶሪያ ሰማይ - ሚያዝያ 5 ለ6 አጥቢያ 2010 ዓ.ም ማለዳ
የሶሪያ ሰማይ - ሚያዝያ 5 ለ6 አጥቢያ 2010 ዓ.ም ማለዳ

ሶሪያ ላይ ትናንት የተካሄደው ጥቃት እጅግ የተዋጣ እንደነበርና ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ሊከናወን እንደማይችል ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ አስታውቀዋል።

ሶሪያ ላይ ትናንት የተካሄደው ጥቃት እጅግ የተዋጣ እንደነበርና ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ሊከናወን እንደማይችል ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ አስታውቀዋል።

ዶናልድ ትረምፕ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት
ዶናልድ ትረምፕ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ባወጡት ትዊት “ተልዕኮው ተፈፅሟል!” ብለዋል። https://twitter.com/realDonaldTrump/status/985130802668294144?ref_src=twsrc%5Etfw&ref_url=https%3A%2F%2Fwww.voanews.com%2Fa%2Fus-britain-france-syria-chemical-weapons%2F4347934.html&tfw_site=voanews

ትረምፕ በሶሪያ ዒላማዎች ላይ የሃገራቸው፣ የእንግሊዝና የፈረንሣይ ጥምር ጥቃት መከፈቱን ትናንት ምሽት ላይ ዋይት ሃውስ ውስጥ ሲያሳውቁ የሦሪያ ጋሻ ጃግሬዎች መንግሥታት ካሏቸው መካከል ሩሲያንና ፕሬዚዳንቷን በተለይ አንስተው ወቅሰዋል።

“በ21013 ዓ.ም. (እአአ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲን እና መንግሥታቸው የሶሪያን ኬሚካል የጦር መሣሪያዎች ለማውደም ዋስትና ሰጥተዋል። አሳድ ሰሞኑን የፈፀሙት ጥቃትና ዛሬ እኛ የሰጠነው አፀፋ ፑቲን ያንን ቃላቸውን ያለመጠበቃቸው ውጤት ነው። ሩሲያ በዚህ የጨለማ መንገድ ከመቀጠልና እንደ ሰላምና መረጋጋት ኃይል የሰለጠነውን ዓለም ከመቀላቀል አንዱን መምረጥ አለባት” ብለዋል።

ይህ ካርታ አሜሪካ፣ እንግሊዝና ፈረንሣይ ሶሪያ ላይ ድብደባ የፈፀሙባቸውን ቦታዎች ያሳያል፤ ሚያዝያ 5 ለ6 አጥቢያ፣ 2010 ዓ.ም.
ይህ ካርታ አሜሪካ፣ እንግሊዝና ፈረንሣይ ሶሪያ ላይ ድብደባ የፈፀሙባቸውን ቦታዎች ያሳያል፤ ሚያዝያ 5 ለ6 አጥቢያ፣ 2010 ዓ.ም.

በመከላከያ መሥሪያ ቤቱ ውስጥ ማብራሪያ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስትሩ ጄምስ ማቲስ ደግሞ “ወሣኝ እርምጃ” ሲሉ የጠሩት ይህ ጥቃት የባሻር አል አሳድን መንግሥት ‘የኬሚካል ትጥቅና አቅም አከርካሪ የሰበረ’ እንደሆነ ተናግረዋል።

“ዛሬ ከአጋሮቻችን ጋር ሆነን ያሳረፍንበት ዱላ አሳድና ነፍሰገዳይ አበጋዞቹ በተጠያቂነት ሊያዙ የሚችሉበትን ሌላ ኬሚካል ጥቃት እንዳይፈፅሙ ግልፅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው” ብለዋል ሚኒስትሩ።

ባለፈው ሳምንት ዱማ ከተማ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን የክሎሪን ጋዝ ጥቃት የምታስተባብለው የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ግን የትናንት ምሽቱን ድብደባ “እጅግ ብርቱ በሆነ ሁኔታ” አውግዘው ለሶሪያ ይበልጥ የተራቀቁ የሚሣይል ትጥቆችን እንደሚልኩ አስታውቀዋል።

ቭላዲሚር ፑቲን፤ የሩሲያ ፕሬዚዳንት
ቭላዲሚር ፑቲን፤ የሩሲያ ፕሬዚዳንት

በትናንት ምሽቱ ጥቃት ወቅት ኤስ-100 እና ኤስ-200 የሚባሉ ሩሲያ ሠራሽ የሆኑ ፀረ-ሚሳይል ተምዘግዛጊዎች ወደ ሶሪያ ይተኮሱ የነበሩ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ሚሳይሎች አየር ላይ እየቀለቡ አምክነዋል ሲል የሶሪያ መንግሥታዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ጀርመን፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያና ጃፓን ሦስቱ ሃገሮች ትናንት ለፈፀሙት ጥቃት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ተስክ “እኛ ከአጋሮቻችን ጋር ከፍትሕ ጎን እንቆማለን” ብለዋል። የሰሜን አትላንቲክ የጦር ትብብር ድርጅቱ ኔቶ ዋና ፀሐፊ የንስ ሽቶልተንበርግ “ኬሚካል መሣሪያን የሚጠቀም ሊጠየቅ ይገባል” ብለዋል።

በመንግሥታቱ ድርጅት የቻይና ቋሚ ተጠሪ ማ ዥአሁ ደግሞ በአካባቢው ውጥረት እንዲረግብና ነገሮች በጥንቃቄ እንዲያዙ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉም ወገኖች ለዓለምአቀፍ ሕግጋት እንዲገዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ አሳስበዋል።

ከአረቡ ዓለም የተባበሩት ገረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያና ካታር ለአሜሪካ መራሹ ጥቃት ድጋፋቸውን አሳውቀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“ሚሺን አካምፕሊሽድ!” - ትረምፕ - “የላቀ ሚሳይል እንልካለን” - ፑቲን
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:44 0:00

የቪኦኤን የቪድዮ ዘገባ ለማየት ከታች ያለውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ።

https://www.voanews.com/a/us-britain-france-syria-chemical-weapons/4348107.html

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሶሪያ ላይ ስለከፈቱት ጥቃት ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ውስጥ ያደረጉትን ሙሉ ንግግር ከታች በተያያዘው ቪድዮ ፋይል ላይ ያገኛሉ።

https://www.voanews.com/a/us-britain-france-syria-chemical-weapons/4347857.html

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስት ጄምስ ማቲስና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጆዜፍ ዳንፎርድ በመከላከያ መሥሪያ ቤቱ ውስጥ የሰጧቸውን ሙሉ ማብራሪያዎች ከከታች በተያያዘው ቪድዮ ፋይል ላይ ያገኛሉ።

https://www.voanews.com/a/us-britain-france-syria-chemical-weapons/4347884.html

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG