በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማክሮን ዋሺንግተን ዲሲ ገቡ


ፎቶ ፉይል:- የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፉይል:- የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዩናይትድ ስቴትስ የሦስት ቀናት ሙሉ መንግሥታዊ ጉብኝት ለማድረግ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ገቡ።

የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዩናይትድ ስቴትስ የሦስት ቀናት ሙሉ መንግሥታዊ ጉብኝት ለማድረግ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ገቡ።

ሚስተር ማክሮን አቀባበል እንደተደረገላቸው ባደረጉት ንግግር ከዩናይትድ ስቴትስ አቻቸውና ከሌሎችም የአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር በምጣኔ ኃብት፣ በንግድ፣ በፀጥታና በሌሎችም የጋራ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ አስታውቀዋል።

ማክሮን አሜሪካ ውስጥ በሚቆዩባቸው ቀናት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ከእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ሽንፈት በኋላም ቢሆን ሶሪያ ውስጥ እንዲሰነባብቱ ፕሬዚዳንት ትረምፕን ለማሳመንና የአውሮፓ ኅብረትን ከአሉሚነምና ከብረት ታሪፋቸው ውጭ እንዲያደርጉም ለመማለድ እንደሚጥሩ ተገልጿል።

“ከጦርነቱ በኋላም አዲሲቱን ሶሪያን መገንባት ይኖርብናል፤ ለዚህ ነው የዩናይትድ ስቴትስ ሚና እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው የምለው” ብለዋል ፕሬዚዳንት ማክሮን ለጉዟቸው ከመነሣታቸው በፊት ፋክስ ኒውስ ለሚባለው የዜና አውታር ፓሪስ ላይ በሰጡት መግለጫ።

“ለሰላምና ለዘርፈብዙነት ዩናይትድ ስቴትስ መተኪያ የሌላት ሃገር ነች” ብለዋል ማክሮን።

“ከሶሪያ የምንወጣ ከሆነ ሜዳውን ለቅቀን የምንወጣው ለኢራንና ለአሳድ እንደሚሆን በቀጥታ መናገር እፈልጋለሁ” ያሉት ሚስተር ማክሮን ሩሲያና ቱርክም ሊጫወቱት የሚችሉት ገንቢ ሚና ሊኖር እንደሚችል አመልክተዋል።

የኢራንን የኒኩሌር መርኃግብር ውል አስመልክቶም ሲናገሩ ምንም እንኳ ፍፁም ነው ባይባልም ለጊዜው ውሉ ባለበት እንዲቀጥል እንደሚፈልጉም ፕሬዚዳንት ማክሮን ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG