በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመረጃ ሣጥኑ ርክክብ ተፈፀመ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት ከሆነውና ትናንት ቢሾፍቱ አቅራቢያ ከወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን ስብርባሪ ውስጥ የተገኘው የመረጃ መዝጋቢ ሳጥን ርክክብ መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ትናንት ቢሾፍቱ አቅራቢያ ከወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን ስብርባሪ ውስጥ የተገኘው የመረጃ መዝጋቢ ሳጥን ርክክብ መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በምርመራው የሚያግዙ ባለሙያዎች ያሉበትን ቡድን ዛሬ ወደ አዲስ አበባ አንቀሳቅሳለች።

በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተመዘገበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጄት አደጋው ከደረሰበት ሰዓት አንስቶ ሙሉ መንግሥቱና የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ሁሉ እየተረባረቡ ቆይተዋል።

በተስፋ ጨለማ ውስጥም “የሚተርፍ ቢኖር” በሚል ተስፋ ሳይቀር ፈልጎ አትራፊ ቡድኖች ተሠማርተው ነበር። በሕይወት የተገኘ ግን ከአይሮፕላኑ ተሣፋሪ አንድም ሰው አልነበረም።

ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁለነኛው /የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጄነራል/
ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁለነኛው /የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጄነራል/

ዛሬ ስላለው ሁኔታ ለቪኦኤ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው አደጋው ከተከሰተ አንስቶ ባለው ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ሌሎችም መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት ሁኔታውን በቅርብ ይዘው እየሠሩ መሆናቸውን አመልክተዋል።

በትራንስፖርት ሚኒስቴር ሥር ያለው የአደጋ ምርመራ ቢሮም ክትትሉን እንደሚያስተባብር እና ዓለምአቀፍ ድጋፍም እየጠበቀ መሆኑን ገልፀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደ አዲስ አበባ ልኳል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የመረጃ ሣጥኑ ርክክብ ተፈፀመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:16 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG