በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ መንግሥት መዘጋት ምንድነው? ለምን?


የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትና ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት /ምሥል ከኢንተርኔት የተገኘ/
የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትና ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት /ምሥል ከኢንተርኔት የተገኘ/

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዛሬ፤ ማክሰኞ - ጥር 28/2019 ዓ.ም. ምሽት ላይ ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ በሃገራቸው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ንግግር ያደርጋሉ። በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በተወካዮች ምክር ቤቱ አፈጉባዔ ናንሲ ፔለሲ መካከል የተፈጠረው መፋጠጥ ለውጥ አላሳየም። ሌላ የመንግሥት መዘጋት ዙር፣ ወይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥጋት አሜሪካ ላይ አንዣብቧል።

የዩናይትድ ስቴትት መንግሥት ባጋጠመው የፖለቲካ መፋጠጥና በዚህ ዘመን በጀት መንጠፍ ምክንያት ለ35 ቀናት ከተዘጋ በኋላ በወዲያኛው ዓርብ ምሽት ተከፍቷል።

ለመሆኑ የዚህ መንግሥት የመዝጋት አባዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ምንድነው? ለምን የዩናይትድ ስቴትስ ፈሊጥስ ሆነ? ጥቅምና ጉዳት ይኖረው ይሆን?

የመዘጋቱ ዳራ፣ ይዘትና መዘዝ ...

በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በተወካዮች ምክር ቤቱ አፈጉባዔ ናንሲ ፔለሲ መካከል የተፈጠረው መፋጠጥ ለውጥ አላሳየም። ፕሬዚዳንቱ ዩናይትድ ሰቴትስ ከሜክሲኮ ጋር በምትዋሰንበት የደቡብ ድንበር ላይ ‘አቆመዋለሁ’ ሲሉ ከ‘ምረጡኝ’ ዘመቻቸው ወቅት አንስቶ ይዘውት የነበረውን የግንብ ወይም የአጥር አቋማቸውን አጠናክረውና አምርረው ቀጥለውበታል። አፈጉባዔዋና ዴሞክራቲክ እንደራሴዎቹ ደግሞ ይህንን የአጥር ነገር መስማት አይፈልጉም። መንግሥቱ ከወር በላይ የተዘጋው በዚሁ ሰበብ ነው። እንደገና ላለመዘጋቱ ዋስትና የለም።

“ከፕሬዚዳንቱ ዛቻና ፉከራ በመነሣት ቢዘጋ አይደንቀኝም” ይላሉ የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ብሩክ ኃይሉ።

ዘገባውንና ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉን ትንታኔ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአሜሪካ መንግሥት መዘጋት ምንድነው? ለምን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:45:22 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG