ዋሺንግተን ዲሲ —
የኬንያ መንግሥትና ተቃዋሚዎቹ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ ትናንት አደጋ በጣሉ ሽብርተኞች ላይ እጅግ ብርቱ የተባለ ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል።
ደሲትዲቱ (DusitD2) በሚባለው የተንደላቀቀ ሆቴልና የተለያዩ ቢሮዎች በሚገኙበት አንድ ተቋም ላይ አጥቂዎቹ በጣሉት አደጋ የተገደለው ሰው ቁጥር 14 መሆኑን የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ አረጋግጠዋል።
ሽብርተኞቹን በሃገራቸው ምድር ላይ የገቡበት ገብተው እንደሚያድኗቸውም ዝተዋል ፕሬዚዳንት ኬንያታ።
የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኤርትራ መንግሥትም ጥቃቱን አውግዘው ዛሬ መግለጫዎችን አውጥተዋል።
ሪፖርተራችን ጆን ታንዛ ከናይሮቢ አጠናቅሮታል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ