በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍተሻ - መድረክና 15ኛ ጉባዔው


ዶ/ር መረራ ጉዲና
ዶ/ር መረራ ጉዲና

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በወዲያኛው ሣምንት ማብቂያ ባደረገው 15ኛ መደበኛ ጉባዔው ማብቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ የብሄራዊ አንድነት መንግሥት እንዲመሠረትና የምርጫ ቦርድ ተዓማኒ ሊሆን በሚችል ሁኔታ እንዲዋቀር ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በወዲያኛው ሣምንት ማብቂያ ባደረገው 15ኛ መደበኛ ጉባዔው ማብቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ የብሄራዊ አንድነት መንግሥት እንዲመሠረትና የምርጫ ቦርድ ተዓማኒ ሊሆን በሚችል ሁኔታ እንዲዋቀር ጠይቋል።

ህገ መንግሥቱ እንዲሻሻል አባሎቻቸው ፍላጎት እንዳላቸው የጠቆሙት ዶ/ር መረራ ጉዲና መድረክ “በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምን” በመሆኑ “...እስከ መገንጠል...” የሚለው ሃረግ ምቾች እንደማይሰጣቸው ተናግረዋል።

ምርጫ ቦርድንም አስመልክቶ ኃላፊው በጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሾም መደንገጉ “ትክክል አይደለም” ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከትግራይ አካባቢ ወከባ እየደረሰብን፣ እንደሕዝብ እየተሰደብንና ጥቃት እየተፈፀመብን ነው የሚሉ ቅሬታዎች መኖራቸውን አስመልክቶ የተጠየቁት የመድረክ ሊቀመንበር “የትግራይ ሕዝብ ድሮም በነበሩ አሁንም ባሉ መሪዎቹ እየተጨቆነ ያለ ያለ ሕዝብ” መሆኑን እንደሚያውቁ ጠቁመው “የትግራይን ሕዝብ እንደመጠለያ አድርጎ ከሌሎች ጋር ለማጋጨት የሚደረግ” ያሉትን አድራጎት እንደሚቃወሙ ተናግረዋል። “ሕዝቡ ሌሎችም እንዲጠየቁ ቢጠይቅ ግን አግባብ ነው” ብለዋል። በሌሎችም በርካታ የወቅቱ ጉዳዮች ላይ ተናግረዋል።

ሙሉውን ቃለ-ምልልስ ከታች ከሰፈሩ በሁለት ክፍሎች ከተያያ ዙትየድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ።

ፍተሻ - መድረክና 15ኛ ጉባዔው - ክፍል 1
please wait

No media source currently available

0:00 0:25:17 0:00
ፍተሻ - መድረክና 15ኛ ጉባዔው - ክፍል 2
please wait

No media source currently available

0:00 0:35:01 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG