በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራዕይ ለኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ገባ


ቪዢን ኢትዮጵያ
ቪዢን ኢትዮጵያ

“ቪዥን ኢትዮጵያ” ወይም “ራዕይ ለኢትዮጵያ” የሚባለው ሲቪክ የምሁራን ስብስብ ሰባተኛ ጉባዔውን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያካሂድ ነው።

“ቪዥን ኢትዮጵያ” ወይም “ራዕይ ለኢትዮጵያ” የሚባለው ሲቪክ የምሁራን ስብስብ ሰባተኛ ጉባዔውን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያካሂድ ነው።

ቡድኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሰበሰብ የመጀመሪያ ጊዜው ሲሆን ለዚህ የሁለት ቀን ጉባዔ ከመላ ዓለም አዲስ አበባ የሚገቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፎችን እንደሚያቀርቡበት ተገልጿል።

በጉባዔው ላይ የሚቀርቡት ሃያ የሚሆኑ ፅሁፎች በመረጃና በአኀዝ የተደገፉ፣ የብዙ ዓመታት ጥናቶች የተካሄዱባቸውና መንግሥት በመጭ ተግባራቱ ውስጥ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ መሆናቸውን የቪዥን ኢትዮጵያን ፕሬዚዳንት ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል።

ጉባዔው የሚካሄደው የፊታችን ታኅሣስ 28 እና ታኅሣስ 29 ሲሆን መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ወደ ቪዥን ኢትዮጵያ ዌብሳይት ‘visionethiopia.org’ በመግባት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።

ለሙሉው ቃለ-ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ራዕይ ለኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ገባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:39 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG