ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የነበረውና በበረራ ቁጥር 302 ተመዝግቦ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ሲነሳ ከትናንት በስተያ ቢሾፍቱ አካባቢ የወደቀውን 737 ማክስ ኤይት አደጋ ተከትሎ የቦይንግ ኩባንያ የአክስዮን ድርሻ ዋጋ በዓለም የገበያ ሠንጠረዦች ላይ ማሽቆልቆሉን ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል።
ተጨማሪ ሃገሮች ማክስ ኤይትን ከአየር ላይ እያወረዱ ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎችም ከአሜሪካ በረራዎች ለጊዜው እንዲታገዱ እየጠየቁ ናቸው።
የአቪዬሽን ቴክኖሎጂው እጅግ መዘመንና በኮምፕዩተር አሠራር መራቀቅ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን እምብዛም የሚያስደስታቸው አይመስል። “አልበርት ኧንሽታይን እንዲያበርረኝ አልፈልግም” ብለዋል። በሌላ በኩል ግን የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ኀዘናቸውን ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የመድን ኩባንያዎች በዋስትና ክፍያ ጥያቄ እየተጨናነቁ ናቸው።
ቦይንግ ደግሞ አሁን ሥራ ላይ ያለውን የአሠራር መመሪያ እንደማይለውጥ አስታውቋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Embed
share
Embed
share
The code has been copied to your clipboard.
The URL has been copied to your clipboard
No media source currently available