በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና ዕረፍት - አቶ ሰሎሞን በቀለ ተሸኙ

አቶ ሰሎሞን በቀለ (ታኅሣስ 1/1935 - ታኅሣስ 30/2011)
አቶ ሰሎሞን በቀለ (ታኅሣስ 1/1935 - ታኅሣስ 30/2011)

ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሯቸው እንቅስቃሴዎች፤ በዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ፣ እንዲሁም በአትላንታ-ጆርጂያ በተለያዩ የሙያ፣ የንግድ፣ የበጎ አድራጎት፣ የድጋፍና ሌሎችም ተግባሮቻቸው የሚታወቁት የአቶ ሰሎሞን በቀለ አስከሬን ዛሬ ተሸኝቷል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሯቸው እንቅስቃሴዎች፤ በዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ፣ እንዲሁም በአትላንታ-ጆርጂያ በተለያዩ የሙያ፣ የንግድ፣ የበጎ አድራጎት፣ የድጋፍና ሌሎችም ተግባሮቻቸው የሚታወቁት የአቶ ሰሎሞን በቀለ አስከሬን ዛሬ ተሸኝቷል።

አቶ ሰሎሞን በቀለ ያረፉት በሰባ ስድስት ዓመት ዕድሜአቸው ሲሆን የዛሬው የሽኝትና የፍትኀት ሥርዓት የተካሄደው ሜሪላንድ በሚገኘው ደብረገነት መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ነው።

አቶ ሰሎሞን በቀለ በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከአዲስ አበባ የንግድ ሥራ ኮሌጅ በሂሣብ አያያዝ ተመርቀዋል። ከዚያም በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ኦፐሬሽኖች ክፍል አገልግለዋል።

ወደ ዩናይትጽድ ስቴትስ በ1960 ዓ.ም. ከገቡ በኋላ በአትላንታ-ጆርጂያ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፍልሰተኛ ሆነዋል።

ከክላርክ አትላንታ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ይዘዋል። በጆርጂያ ስቴት ዩኒቨርሲቲም የዶክትሬት ጥናታቸውን ለማካሄድ ገብተው ለሁለት ዓመት ተከታትለዋል። ከጆን ማርሻል ትምህርት ቤት በሕግ ዶክትሬት ዲግሪ መያዛቸውን የሕይወት ታሪካቸውን ለመዘከር የወጣ ፅሁፍ ይናገራል።

አቶ ሰሎሞን በቀለ (ታኅሣስ 1/1935 - ታኅሣስ 30/2011)
አቶ ሰሎሞን በቀለ (ታኅሣስ 1/1935 - ታኅሣስ 30/2011)

አቶ ሰሎሞን በቀለ አትላንታ ላይ የመጀመሪያውንና ዛሬ እጅግ ግዙፉ የሆነውን የታክሲ አገልግሎት ኩባንያ /በአ.ዘ.አ./ በ1976 ዓ.ም. መሥርተዋል።

በኢትዮጵያ ረዳት ለሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ሲያደርጓቸው በነበሩ እንቅስቃሴዎች ሜሪ ጆይና ወገኔ ከሚባሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር ሲተባበሩ ከመቆየታቸው ሌላ በቀጥታም የረዷቸው ሰዎችና ድርጅቶች ብዙ መሆናቸው ይነገርላቸዋል።

በአትላንታ ከየሳህሊተ-ምኅረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን፣ በዋሺንግተን ዲሲም ከደብረገነት መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን መሥራቾች አቶ ሰሎሞን በቀለ አንዱ ነበሩ።

ስለፍትሕና እኩልነትም በነበራቸው አቋም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከኢዴኃቅ እስከ ቅንጅት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የነበሩ እንቅስቃሴዎችንም በአካልም በገንዘብም ሲደግፉ መቆየታቸው ይታወሳል።

ከወንድማቸው ከአቶ መርዕድ በቀለ ጋር የተደረገውን አጭር ቃለ-ምልልስ ያካተተ ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዜና ዕረፍት - አቶ ሰሎሞን በቀለ ተሸኙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG