ኢትዮጵያ ሳተላይት የፊታችን መስከረም ውስጥ ልታመጥቅ ነው።
በአንዳንድ ካቶሊካዊያን ቀሳውስት ዘንድ ይታያል ያሉት የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትና ግብረሥጋ ጠባይ በብርቱ እንደሚያሳስባቸው የሮማው ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ፍራንሲዝ አስታውቀዋል።
ሰሞኑን ላረፉት የዩናይትድ ስቴትስ አርባ አንደኛ ፕሬዚዳንት ለነበሩት ለጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ አሸኛኘት እየተደረገ ነው። አስከሬናቸው በብሄራዊው ካቴድራል አርፎ የፀሎትና የዝክር ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ተጠናቅቆ በመጭው ሣምንት ውስጥ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ አስታውቀዋል።
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ ወደ ሰላማዊ ትግል መግባቱን ያሳወቀው ትጥቁን ፈትቶ መሆኑን ቃል አቀባዩ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ወደ ሰላም የተቀላቀሉትን የኦብነግ ታጣቂዎች ሰዉ ጂግጂጋ ላይ የተቀበላቸው ከአይሮፕላን ማረፊያው አንስቶ በመንገዶች ግራና ቀኝ ተሰልፎ እንደነበረ የገለፁት ቃል አቀባዩ ሄርሞጌ በእውኑ “የሞቀና የደመቀ ነበር” ብለውታል አቀባበሉን።
በትጥቅ ትግል መቀጠል የሚፈልግ ካለ መንግሥት በሰላም አሳምኖ ለመመለስ ጥረት ማድረግ አለበት፤ ካለበለዚያ “መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ግዴታ ስላለበት በወሰነበት መንገድ ሁኔታውን መቆጣጠር ይችላል” ብለዋል የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ።
የአሜሪካ ድምፁ ተወልደ ወልደገብርዔል ወደ ኤርትራ ተጉዞ የተለያዩ ሥፍራዎችን ተመልክቷል።
ትውልደ-ሶማሌዪቱ ኢላን ኦማር እና ከኮሎራዶ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ለኮንግረስ ሲመረጥ የመጀመሪያ የሆኑት የኤርትራ-አሜሪካዊያን ልጅ ጆዜፍ ንጉሤ የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ሆነው ተመርጠዋል።
ዛሬ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ የአማካይ ዘመን ምርጫ እየተካሄደ ነው።
ወደ ጋምቤላ ክልል አቦቦ ወረዳ ሄደው የነበሩ ስምንት ጋዜጠኞች “በመንግሥት ባለሥልጣናት ተደበደብን፣ ተዋከብን፣ ታገትን፣ ያለአግባብ በቁጥጥር ሥር ዋልን” ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል። የወረዳው አስተዳደር አስተባብሏል።
ለሐረር ከተማ ይደርስ የነበረው የውኃ አቅርቦት የሁለት ማምረቻና ማከፋፈያዎች ሥራና አቅርቦት በአካባቢዎቹ የሚገኙ ናቸው በተባሉ ሰዎች ከተስተጓጎሉ በኋላ በተደረጉ የተለያዩ ጥረቶች “በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ መፍትኄ ይገኛል” ሲሉ የሐረሪ ክልል የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አስታውቀዋል።
ኤርትራ ከቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን አጋጣሚዎችና ክስተቶች ልትማር ይገባታል የሚል መልዕክት ያለው ፅሁፍ የፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂን አትኩሮት እንዲያገኝ በቅርቡ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ አውጥተዋል።
ኢሕአዴግ ባለፈው ሣምንት ውስጥ ለሦስት ቀናት ያካሄደውን አሥራ አንደኛውን ድርጅታዊ ጉባዔውን ከትናንት በስተያ ቅዳሜ በይፋ ዘግቷል። ጉባዔው የተጠናቀቀው ባለፈው ዓርብ ባወጣው የአቋም መግለጫ ነበር።
በኒው ዮርክ ታላቁ ማንሃታን ክፍለ-ከተማ ከማዕከሉ ብዙም ሳይርቅ በተዘረጋው ሐርለም ቀበሌ ውስጥ 138 ዌስት 138ኛው መንገድ ላይ የቆመ ውብ የድንጋይ ጥርብ ሕንፃ ግንባታው ተጠናቅቆ የዛሬ ሥራውን ከጀመረ ዘንድሮ ልክ ዘጠና አምስት ዓመት ሞላው።
የአፍሪካ ቀንድ “የአፍሪካ ተስፋ እየሆነ ነው” ብለዋል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባ ሦስተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፡፡
ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዘንድሮው የመንግሥታቱ ድርጅት ሰባ ሦስተኛ ጉባዔ መክፈቻ ላይ አይገኙም፡፡
ቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በቅርቡ ባወጡት አንድ ፅሁፍ የአካባቢውን ጂዖ ፖለቲካዊ መስተጋብርና ተፅዕኖ አሳዳሪ ያሏቸውን ዓለምአቀፍ የዲፕሎማሲ፣ ምጣኔኃብታዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ተንትነዋል።
ኢትዮጵያና ኤርትራ ከአረቢያ ልሣነ-ምድር መንግሥታት ጋር ያሉበት የተሟሟቀ ግንኙነት ምናልባት ኢትዮጵያን ወደ የመኑ ጦርነት ይጎትታት ይሆን? የሚል ሥጋት የቀሰቀሰባቸው ጥቂት አይደሉም።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሐምሌ / 2010 ዓ.ም መገባደጃ ላይ በዩናይትድ ስቴትስ ላደረጉት የአምስት ቀናት ጉብኝት የአሜሪካ ድምፅ የተሟላ ሽፋን ሰጥቷል።
ተጨማሪ ይጫኑ