በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቀን አሥራ ስምንት


ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር ሃገሪቱ ከሜክሲኮ ጋር የምትዋሰንበት የደቡብ ድንበር አካባቢ ያለው ሁኔታ የማይቀር “የሰብዓዊና የብሄራዊ ፀጥታ ቀውስ” ነው የሚል ዕምነት ለማሥረፅ በብርቱ እየገፋ መሆኑ ተገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር ሃገሪቱ ከሜክሲኮ ጋር የምትዋሰንበት የደቡብ ድንበር አካባቢ ያለው ሁኔታ የማይቀር “የሰብዓዊና የብሄራዊ ፀጥታ ቀውስ” ነው የሚል ዕምነት ለማሥረፅ በብርቱ እየገፋ መሆኑ ተገልጿል።

የፕሬዚዳንቱ አቋም ከሕዝብ እንደራሴዎቹ ጋር ለገቡበት የወሰን አጥር ግንባታ ሃሣባቸው ድጋፍ ለማግኘት እንደሆነ ነው የሚሰማው።

በዚሁ በፕሬዚዳንቱና በእንደራሴዎቹ መካከል በተፈጠረው ፍጥጫ ምክንያት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በከፊል ከተዘጋ ዛሬ አሥራ ስምንተኛ ቀኑን ደፍኗል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ይህንኑ የደቡብ ድንበር ግንብ ሃሣባቸውን ለማስረገጥ አስበውበታል የተባለ ንግግር ዛሬ ምሽት ላይ በቴሌቪዥን ያደርጋሉ ተብሏል። ከነገ በስተያ ሐሙስ ደግሞ ወደ ወሰኑ አካባቢ እንደሚሄዱ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ግን የተወካዮች ምክር ቤቱ “ለፕሬዚዳንት ትረምፕ የጠየቁትን የግንብ ማሠሪያ ወጭ ቢፈቅድላቸው የተሣሣተ እርምጃ ይሆናል” ሲሉ ዛሬ ኒው ዮርክ ላይ ለተሰበሰቡ ታዳሚዎች ንግግር ያደረጉት የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤቱ ዴሞክራቲክ መሪ ቸክ ሹመር አመልክተዋል።

“ሃገር ማስተዳደር እንዲህ አይደለም። ቡጢ ጨብጠህ ጠረጴዛ እየደበደብክ እኔ ያልኩት ካልሆነ እያልክ ለሚሊዮኖች መጎዳት ምክንያት በመሆን አይደለም። ሕገመንግሥቱ እንዲያ አይልም። ምርጫዎች መዘዝ እንደላቸው ይታወቃል። ሪፐብሊካኑ የሕግ መምሪያውንም የሕግ መወሰኛውንም ተቆጣጥረው በነበሩበት ጊዜ እንኳ ፕሬዚዳንቱ ይህንን ግንብ የማቆም ሃሣባቸውን ማስፀደቅ አልቻሉም። ምክንያቱም መጥፎ ሃሣብ መሆኑን እንደራሴዎቹ ያውቁ ስለነበረ ነው። አሁን ታዲያ ምንም እንኳ ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ምርጫ የሕዝብ ይሁንታ ተነፍገው የተወካዮች ምክር ቤቱን ከእንግዲህ ባይቆጣጠሩትም መንግሥቱን ዘግተውታል” ብለዋል ሴናተር ሹመር።

በፕሬዚዳንቱና በዴሞክራቲክ እንደራሴዎቹ መካከል በተፈጠረው መፋጠጥ መንግሥቱ ከተዘጋ ወደ ሦስተኛ ሣምንቱ ቢገባም እስከአሁን ከተካሄዱ ድርድሮች የተጨበጠ ተስፋ ሰጭ ውጤት የለም።

የዩናይትድ ስቴትስን ሩብ መንግሥት የዘጋው የአሁኑ ሁኔታ ወደ ፍፃሜው የመጠጋት አዝማሚያም እየታየ አይደለም።

ስምንት መቶ ሺህ የሚሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሠራተኞች አንድም ከሥራቸውና ከክፍያ ውጭ ሆነዋል፤ አልያም ያለክፍያ እየሠሩ ናቸው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ቀን አሥራ ስምንት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:14 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG