ባለፈው ዕሁድ ቢሾፍቱ አቅራቢያ በወደቀው የአይሮፕላን አደጋ ስለሞቱት ዜጎች ዛሬ (ዕሁድ) ኢትዮጵያ ውስጥ በተከናወነ ሥነ-ሥርዓት ላይ የወጣ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሰው የሃገሪቱን ብሄራዊ ባንዲራ የለበሱ 17 ባዶ የአስከሬን ሣጥኖችን አጅቧል።
የሟቾች ቤተሰቦች ከሆኑት መካከል አንዳንዶች “በኀዘን ራሳቸውን ስተዋል” ሲል አሶሼትድ ፕሬስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
በአይፕላኑ አደጋ ላይ ያለቁት ሰዎች አከሬኖችን የመለየቱ ሂደት ረዥም ጊዜ ስለሚወስድ የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ለሞቱት 157 መንገደኞች ቤተሰቦች ከአደጋው ሥፍራ አፈር የተሞላ ኬሻ ትላንት መስጠት ጀምረዋል።
የሟቾች ቤተሰቦች አይሮፕላኑ ከተከሰከሰበት ቦታ የተወሰደ አንድ ኪሎግራም አፈር እንደተሰጣቸው አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ኢቲ-302 አደጋ ላይ ካለቁት ሰዎች መካከል የ36 ሃገሮች ዜጎች ይገኙባቸዋል።
በአደጋው ሕይወታቸው ከጠፋው 149 መንገደኞች መካከል ለጉባዔ ወደ ናይሮቢ ይጓዙ የነበሩ የሰብዓዊ ረድኤት ሠራተኞችም ነበሩባቸው።
ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ