በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዓለም ታላላቅ አሳቢዎች አንዱ ...

Protest in Skopje opposing the French proposal for EU membership negotiations, Skopje, Saturday 07/16, North Macedonia
Protest in Skopje opposing the French proposal for EU membership negotiations, Skopje, Saturday 07/16, North Macedonia

“... አብይ አሕመድ ጥረቶቻቸው እንደሚሳኩላቸው የብዙዎች ተስፋ ነው ...” ሲል ፎረን ፖሊሲ ፅፏል።

ዋና ፅሕፈት ቤቱ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ የሆነውና በዓለምአቀፍ አካባቢያዊና የወቅቱ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው ፎረን ፖሊሲ መፅሔት በዚህ ዓመት ልዩ ዕትሙ የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ከዓለም መቶ ታላላቅ አሳቢዎች አንዱ አድርጎ አውጥቷል።

አብይ አሕመድ (ዶ/ር) - የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር - የገፅ ንድፍ በ "ፎረን ፖሊሲ" መፅሔት
አብይ አሕመድ (ዶ/ር) - የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር - የገፅ ንድፍ በ "ፎረን ፖሊሲ" መፅሔት

በየዓመቱ ስድስት ልዩ ዕትሞችን የሚያወጣው ላለፉት ሃምሣ ዓመታት የቆየውና አሁንም ዕለታዊ ሁኔታዎችን ዌብሳይቱ ላይ በየዕለቱ የሚዘግበው ፎረን ፖሊሲ መፅሔት ስለዶ/ር አብይ ስኬቶች ካሠፈረው መካከል ወደ ሥልጣን በዘለቁ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ በአካባቢው ሰላም ያወረደውንና የተለያዩ ቤተሰቦችንም ያገናኘውን የኤርትራ ጋር የፈጠሩትን ስምምነትና ዕርቅ በቀዳሚነት አንስቷል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “... በአሁኑ ጊዜ ሃገራቸው ውስጥ እየተስተዋለ ያለውን የራሣቸውን የመከፋፈል ችግር በማከም ላይ አተኩረዋል” ብሏል ፎረን ፖሊሲ።

“በአመፆችና በሁከቶች ተውጣ ከነበረችው ኦሮምያ ኢትዮጵያን ለመምራት የመጀመሪያው ሰው የሆኑት አብይ አሕመድ ጥረቶቻቸው እንደሚሳኩላቸው የብዙዎች ተስፋ ነው” ሲልም ፎረን ፖሊሲ አክሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG