አዲስ አበባ —
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞውን የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሽን በነፃ አሰናበታቸው፡፡ የወቅቱን የዓረና ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ ጉዳይንም እንዲቋረጥ አዘዘ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ረፋዱ ላይ በአሰማው ውሳኔ የቀድሞውን የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሽን እንዲከላከሉ በተበየነው መሠረት የአቀረቧቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች እንደመረመረ አትቶ ክሱን በበቂ ሁኔታ ተከላክለዋል ሲል በነፃ አሰናብቷቸዋል፡፡
ጠበቃው አቶ አምሃ መኮነን ጉዳዩን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ