አዲስ አበባ —
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ቤት ስለሞቱት አቶ አየለ በየነ ሞትና የሞታቸውን ምክንያት ከሚመለከተው ሆስፒታል ማስረጃ አንዲያቀርብ፣ ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ጥብቅ ትዛዝ ሰጠ፡፡
ክሱም እንዲቀጥል ተወሰነ፡፡ የትዛዙን አፈፃፀም ውጤት ለመጠበቅ ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ተመሳሳይ ትዕዛዝ ቀደም ብሎ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ትናንት በዋለው ችሎት እንደተስተዋለው የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የተሰጠውን ትዕዛዝ አልፈፀመም፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ