በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አቶ በቀለ ገርባ በዋስ ሊፈቱ አይገባም” - የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ


አቶ በቀለ ገርባ
አቶ በቀለ ገርባ

የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ በቀለ ገርባ በዋስ ሊፈቱ አይገባም የሚል መከራከሪያ አቀረበ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ በቀለ ገርባ በዋስ ሊፈቱ አይገባም የሚል መከራከሪያ አቀረበ፡፡

ጉዳዩን እየመረመረ የሚገኘው ፍ/ቤት፣ የሁለቱን ወገኖች ክርክር አይቶ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ቆርጧል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት፣ በነጉርሜሳ አያና መዝገብ ላይ ብይን ከሰጠ በኋላ የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው አቶ በቀለ ገርባ፣ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ላቀረቡት ጥያቄ ዓቃቤ ሕግ ዛሬ በፁሑፍ ተቃውሞውን አቅርቧል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ክርክር መሰረት፣ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች ሃያ ሁለት ተከሳሾች ክስ ሲመሰረትባቸው ዋስትና ተከልክለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“አቶ በቀለ ገርባ በዋስ ሊፈቱ አይገባም” - የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:12 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG