ዋሺንግተን ዲሲ —
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት አቶ በቀለ ገርባ ያቀረቡትን የዋስ መብት ጥያቄ ዛሬ ውድቅ አደረገ፡፡
አቶ በቀለ ገርባ ውሳኔው ምንም እንዳላስደነቃቸው እና ይጠብቁት የነበረ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ገለፁ፡፡ ጠበቆቻቸው ይግባኝ እንደሚሉ አሳወቁ፡፡
ለሳምንታት ሲንከባለል የቆየው አቶ በቀለ የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዳደረገው በዛሬው ችሎት አስታወቀ፡፡
ፍርድ ቤቱ የሁለቱምን ወገኖች እንደመዘነ በሚያሳይ መልኩ፣ ትችቱን ለችሎቱ አሰምቷል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ