አዲስ አበባ —
የፌደራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በኦሮሞ ፌዳራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ ሊቀ መንበር በዶ/ር መረር ጉዲና ላይ አሥር ሲዲ ተጨማሪ ማስረጃ ማቀረቡ ተሰማ። የተከሳሹ ጠበቃ ተቃውሞአቸውን ለፍርድ ቤት ማቅረባቸውን ይናገራሉ።
ፍርድ ቤቱ በዚሁ ክርክር ላይ ታህሳስ 19 ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ አሥር የሲዲ የድምፅ ከምስል ተጨማሪ ማስረጃ እንዳሉት በመግለፅ ጉዳዩን ለያዘው ፍርድ ቤት አመለከተ፡፡ ዓቃቤ ሕግ ቀደም ሲል ኅዳር 22 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት እስከ ዕለቱ ድረስ በኦፌኮ ሊቀመንበር በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ያቀረበው የምስክሮችም ሆነ ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎች በቂ መሆናቸውን በመግለፅ፣ ፍ/ድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ “ይከላከል” የሚል ብይን እንዲሰጥለት ጠይቆ የነበረ ቢሆንም አሁን ያቀረባቸው አሥር የድምፅ ከምስል ማስረጃ ሲዲዎች አያይዞ ያስገባው ማመልከቻ ግን ይሄንን የሚቃረን ይመስላል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ