በቅርብ ግዜ ከእስር የተፈቱትን እስክንድር ነጋን፣ አንዷለም አራጌንና ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ አያሌ ሰዎች አዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በኮማንድ ፖስቱ ትዛዝ ታስረው እንደሚገኙ ታወቀ። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በኮማንድ ፖስቱ ትዛዝ ከመታሰራቸው የተለየ ሌላ መረጃ እንደሌለው ተናግሯል።
ከዋልድባ ገዳም ተይዘው በእስር የሚገኙት ሁለቱ መነኮሳት ሀይማኖታዊ ልብሳቸውን ከመልበስ እንዳይከለከሉ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ጂቡቲ የኢትዮጵያ ዋንኛ የወጭና የገቢ ንግድ በር ሆና እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቀ፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ አሥራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት በቂሊንጦ እሥረኛ ማቆያ ቃጠሎ በተጠረጠሩት በእነ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ ብይኑን ሳያሰማ ቀረ፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ “ሰሞኑን ሞያሌ ውስጥ የንፁሃን ዜጎችን ሕይወት አጠፉ” ያላቸው የመከላከያ ሠራዊት አባላት በግልፅ ችሎት ፊት ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።
በደቡብ ኦሮሚያ በሞያሌ ከተማ ትናንት ማታ አንድ ሰው ባልታወቁ ሰዎች ተመቶ መሞቱና ሌላው ደግሞ በጥይት ተመቶ መቁሰሉ ተሰማ። ከሞያሌ ከተማ አራት ቀበሌዎች እጅግ በርካታ ነዋሪዎች መሰደዳቸው ታወቀ። እስካሁን ለማረጋጋት በተወሰደው እርምጃም በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንድ የኮማድ ፖስቱ ጽ/ቤት ተወካይ አስታወቁ።
ሩሲያ ግጭቶች ያለምንም ጣልቃ ገብነትና ሁሉን ዓቀፍ በሆነ ውይይት እንዲፈቱ እንደምታበረታታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ አስታወቁ፡፡
ከኮንሶ የአስተዳደር እርከን ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የተያዙ ሰዎች አብዛኞቹ ዛሬም በእሥር እንደሚንገላቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ከእሥር መፈታቱ ተሰማ፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ሕገወጥ ያላቸው አካላት የሕዝብን ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ሞክረዋል ሲል አስታውቋል።
ኢህአዴግ ሀገራችንን ካስገባት ቀውስ ውስጥ የማውጣት ብቃት የለውም ሲል የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ አንድነት መድረክ መግለጫ አወጣ፡፡
የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ/ኢራፓ/ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ ለማዘጋጀት ለሀገር ውስጥ የፖለቲካ ድርጅቶች ጥሪ አቀረበ፡፡
ኢትዮጵያ “ገብታበታለች” ካሉት “ውስብስብ ፖለቲካዊ ቀውስ” እንድትወጣ - ዓለምአቀፍ ጉባዔ እንዲዘጋጅ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድና ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አቀረቡ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሞቱ አራስ ሕፃናት ቁጥር ከዓለም ድሃ ሃገሮች አማካይ በላይ እንደሆነ ተገልጿል።
በደቡብን ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በሲዳማ ዞን የበንሳ ወረዳ ፖሊስ አሸባሪዎችን አሳፍራችሁ ወደ ከተማዋ አስገብታችኋል በሚል ሁለት ሰዎችን ማሰሩን የሲዳማ ሃርነት ንቅናቄ አስታወቀ፡፡
በመገናኛ ብዙኃን የማይታወቁ ብዙ እሥረኞች ዛሬም በወህይኒ ቤት እንደሚገኙ ተነገረ፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሊፈቱ የሚገቡ አባሎቻቸው ዛሬም እንዳልተፈቱ አስታወቁ፡፡
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከድርጅት የመሪነት መንበራቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣናቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ይፋ አደረጉ፡፡
ረዥም ዓመት ተፈርዶባቸው ወይኅኒ የነበሩት እነ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ አሕመድ ሙስጠፋ፣ አሕመዲን ጀበልና ሌሎች እስረኞች ዛሬ አመሻሹ ላይ ተፈቱ፡፡
በኦሮምያ ከተሞች ትናንት የተጀመረው የግብይት ዕቀባና ሥራ የማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን የተለያዩ ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ፓርቲያቸው ከኦሮሚያ ገዥ ኦህዴድ ለመነጋገር መወሰኑን ዶ/ር መረራ ጉዲና አስታወቁ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ