አዲስ አበባ —
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሞቱ አራስ ሕፃናት ቁጥር ከዓለም ድሃ ሃገሮች አማካይ በላይ እንደሆነ ተገልጿል።
የጨቅላ ሕፃናትን ሕይወት ለመታደግ ዓለም ሊሠራ የሚገባውን አልሠራም ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት - ዩኒሴፍ ከስሷል።
ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ባለ ዝቅተኛ ገቢ በሚባሉ ሃገሮች ውስጥ ከሚወለዱ አንድ ሺህ ሕፃናት ሃያ ሰባቱ እንደሚሞቱ፣ በበለፀጉት ሃገሮች ውስጥ ግን ከሺህ አራስ ሕፃናት የሚሞቱት ሦስት መሆናቸውን አመልክቷል።
በኢትዮጵያ አዲስ ከሚወለዱ አንድ ሺህ ሕፃናት ሃያ ዘጠኙ እንደሚሞቱ ዩኒሴፍ አክሎ ጠቁሟል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ