ወደ ሥልጣን ኃላፊነት ከመጡ በኋላ የመጀመሪያው የሆነውን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ጠ/ሚ አብይ አሕመድ የርሳቸውም ሆነ የድርጅታቸው ፍላጎት በኢትዮጵያ በዕውነተኛ ምርጫ ተመርጦ ማገልገል እንደሆነ ገልፀዋል። የምርጫ ጊዜው እንዲተላለፍ እንደማይፈልጉም ተናግረዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ ፍላጎቶችን በተገቢውና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለሟሟላት በሥራው የተሰማሩ ሁሉ ቁርጠኝነታቸውን ከፍ እንዲያደርጉ በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በኢትዮጵያ ኃላፊ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ዓቃቤ ሕግ በቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ ያቀረበው የምርመራ መዝገብ የተሟላ ባለመሆኑ ክስ መመስረት እንዳልቻለ አስታወቀ፡፡
በቴፒ ከተማ ዛሬ ተቀስቅሶ የነበረው አለመረጋጋትና ውጥረት መርገቡ ተነገረ፡፡
ዛሬ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችንና ሁከቶችን ለመግታት የኢህአዴግ የካድሬ አስተዳደር መለወጥ አለበት ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ አስታወቀ፡፡ በሚቀጥለው ሀገርቀፍ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለመመስረት ከወዲሁ የብሄራዊ አንድነት መንግሥት እንዲቋቋምም ጠየቀ፡፡
ዛሬ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችንና ሁከቶችን ለመግታት የኢህአዴግ የካድሬ አስተዳደር መለወጥ አለበት ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ አስታወቀ፡፡
“ሶማሌን እናድን” ብሎ ራሱን የሚጠራ ማኅበር ሁለቱ አባላቱ በሶማሌ ክልል የሽግግር መንግሥት መቋቋም አለበት ሲሉ ለቪኦኤ ተናገሩ፡፡ ማኅበሩ በአሁኑ ጊዜ በክልል ሰላምን ለማጠናከር ከፌዴራል መንግሥቱ ጎን እንደሚቆም አረጋግጠው የክልሉን አስተዳዳሪዎች ግን ሕዝቡ እንዲመርጥ አሳሰቡ፡፡
የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በምክትል ኮሚሺነር ግርማ ካሳ እና በሌሎች አሥር የፖሊስ አባላት የዋስትና ጥያቄ ብይን ሰጠ፡፡
በአዲስ አበባ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በተሰናዳ የሕዝብ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ፈንጅ አፈንድተዋል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎች ላይ አቃቢ ህግ ክስ አደራጅቶ እንዲያቀርብ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፈቀደ።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አንቀፅ 39 ሀገር ለማፍረስ የተቀመጠ ድንጋጌ ነው ሲል ኮነነ፡፡ ይህ ድንጋጌ እንዲሻርም ጠይቋል፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣኖች አዲሱን የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ ሁከት እና ብጥብጥ ይቀሰቅሳሉ ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሰ፡፡
በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን ተርጫና ዋካ በተባሉ ከተሞች በክልሉ ቴሌቨዥን ተሰራጭቷል በተባለ የተሳሳተ ዜና ሳቢያ፣ ትናንት የሰው ሕይወት እያጠፋና የአካል ጉዳት ያስከተለ ተቃውሞ እና ሁከት ተቀስትሶ ዋለ፡፡
ዓለምቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት /ግሎባል አልያንስ ፎር ዘ ራይት ኦፍ ኢትዮጵያንስ/ የተሰኘ ድርጅት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ክልል ለተፈናቀሉ፣ የጌድዮ፣ የወላይታ እና የጉራጌ ተዋላጆች የግማሽ ሚሊዮን ብር ዕርዳታ መስጠቱ ታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ ከጥቂት ወራት በፊት ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ አያሌ ለውጦችን እያስተናገደች መሆኗን በኢትዮጵያ የዩኤስ አሜሪካ አምባሳደር አስታወቁ፡፡
የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ የብዙሃን መገናኛ ድርጅት እስከ ግማሽ ቢሊዮን ብር ሊያስገኝ የሚችል የገንዘብ ማሰባሰቢያ በዓል እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ።
ሰማያዊ ፓርቲ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ወደ ቀድሞ መልኩ እንዲመለስ ጥሪ አቀረበ፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት ዶ/ር አብይ አሕመድ በጠ/ሚኒስትርነት ተሹመው የመጀመሪያውን የመሪነት ንግግራቸውን ሲያደርጉ፣ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ልብ ማርከዋል ቀልብም ስበዋል። ይህ ስሜት እስከዛሬም ይበልጥ እየጋለ እንደሚሄድም ብዙዎች ይናገራሉ።
ኤርትራ በኢትዮጵያ የነበራትንና ከበርካታ ዓመታት በፊት የተዘጋ ኤምባሲዋን ዛሬ ከፈተች።
ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ለመሩት የሉዑካን ቡድን በአዲስ አበባ እጅግ የደመቀ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ጠብቋቸዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ