በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ሲደርሱ የሞቀ አቀባበል ጠብቋቸዋል

አዲስ አበባ ውስጥ ከተሰቀሉ ምስሎች አንዱ
አዲስ አበባ ውስጥ ከተሰቀሉ ምስሎች አንዱ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ጠብቋቸዋል።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ጠብቋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት ኤርትራን ሲጎበኙ ባደረጉላቸው ግብዣ ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከመድፍ ተኩስ እስከ ቤትመንግስት የመቀበያ ምሳ ግብዣ የደመቀ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ፤ ባለሥልጣናት ፣ የኃይማኖት አባቶች ፣የኪነጥበብ ባለሞያዎችና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ አቀባበሉን በጭፈራ አድምቆታል።

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን በቀጥታ ወደ ቤተመንግስት አምርተው የምሳ ግብዣ እንደተደረገላቸው ታውቋል።

ከምሳ ግብዣው በኋላም በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ፈረስ ከእነ ጋሻና ጦሩ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ፈረስ ከእነ ጋሻና ጦሩ ስጦታ ተበረከተላቸው። #Ethiopia #Eritrea #VOAAmharic (መረጃና ፎቶው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ የተገኘ ነው)
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ፈረስ ከእነ ጋሻና ጦሩ ስጦታ ተበረከተላቸው። #Ethiopia #Eritrea #VOAAmharic (መረጃና ፎቶው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ የተገኘ ነው)

(መለስካቸው አመሐ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን አቀባበሉን በተመለከተ አነጋግረነዋል)

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ሲደርሱ የሞቀ አቀባበል ጠብቋቸዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG