በኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ የሉዑካን ቡድን ነገ አዲስ አበባ እንደሚገባ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የመጀመሪያዎቹ 1መቶ የሥልጣን ቀናት ትልቁ ዲፕሎማሲያዊ ስኬታቸው፣ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላም ሊያሰፍን የሚችል ስምምነት ማድረጋቸው እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መካከል ባለው ግንኙነት የታየው ለውጥ ለሁለቱ ሀገሮች ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ትልቅ የተስፋ ምልክት ነው ብለዋል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮን ጉተሬዥ። ሁለቱ ሀገሮች ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚጠይቁትን ሁሉ ለመርዳትም ድርጅቱ ዝግጁ መሆኑንም ዋና ፀኃፊው ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ፓርላማ ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን፣ ኦነግን፣ ኦብነግን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ዝርዝር ሰረዛቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ መሪዎችን አነጋገሩ፡፡ ለአለፉት ዓመታት የተከሰቱ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ሀሳብ እንዲያቀርብም ዘጠኝ አባላት ያሉት አንድ ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡
ኢትዮጵያ አዲስ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ ለማሰናከል፣ ያልታደሰውና የአሮጌው ዘመን ቁማርተኞች ያሏቸው ኃይሎች ደባ እየሰሩ መሆናችውን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ለተሰበሰበው ሕዝብ ይፋ አደረጉ፡፡
የባህር ዳር ነዋሪዎች ለጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ በባህር ዳር ስታድዬም
ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ የጣለበት ዕድል በከንቱ እንዳይባክን ሲል ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አሳሰበ፡፡
የመላው አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ ሰማያዊ ፓርቲና ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሰኔ 16 ቀን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ድጋፍ ለመስጠት በወጣው ሕዝብ ላይ የተሰነዘረውን የቦንብ ጥቃት አወገዙ፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍ ወደ መስቀል አደባባይ የተመመው ሕዝብ - አዲስ አበባ
"ኢትዮጵያ ወደ ቀደመው ገናናነቷ ትመለሳለች" ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ ድጋፉን ላሳያቸው አደባባይ ለወጣው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ ተናገሩ፡፡
ነገ በአዲስ አበባ ከተማ “ዲሞክራሲን እናበርታ” በሚል ቃል በሚካሄደው ግዙፍ የድጋፍ ሰልፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለው እንደሚገኝ፣ አስተባባሪዎ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ከጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ለመወያየት እየጠበቁ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በሀዋሳ እና በዙሪያዋ ለተፈጠረ ግጭት መንስዔው በትክክል እንደማይታወቅ ተነገረ፡፡
የመልካም አሰተዳደር ችግር ከአድራጎቶቻቸው ሊጠበቁ የሚገባቸው የፖለቲካ ነጋዴዎች የሚፈጥሩት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ተናግረዋል።
ትልቅ ሀገራዊ አማራጭ የፖለቲካ ሃይል የሚያደራጅ የጋራ ኮሚቴ መዋቀሩን ሰማያዊ ፓርቲና የኮሚቴው አባላት አስታወቁ።
በአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ምክንያት ከይዞታቸው የተፈናቀሉ አርሶአደሮች ባላቸው አነስተኛ መሬት ራሳቸውንና ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል የተባለ አንድ የንግድ ሥራ ድርጅት መቋቋሙ ታውቋል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አሳሪ ነው ያለውን የአልጀርሱን ሥምምነት የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ መቀበሉ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው አለ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ