በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ በኢትዮጵያ የነበራትን ኤምባሲ ከፈተች


ኤርትራ በኢትዮጵያ የነበራትንና ከበርካታ ዓመታት በፊት የተዘጋ ኤምባሲዋን ዛሬ ከፈተች።

አሥመራ የአዲስ አበባ ኤምባሲዋን ለመክፈ የወሰደችው እርምጃዋ ዜና ይፋ የተደረገው ሁለት አሥርታት ለዘለቀው የጎረቤታች ወታደራዊ ፍጥጫ ማብቂያ ያደረገው የሰላም ስምምነት በተፈረመ አንድ ሳምንት ውስጥ ነው።

መሃል አዲስ አበባ የሚገኘውን የኤርትራ ኤምባሲ ቁልፍ፤ በደማቅ አቀባበል የታጀበውን የሦሥት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ለተመለሱት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ (አዲስ አበባን ከመልቀቃቸው አስቀድሞ) የሰጡት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ናቸው።

ሁለቱ አገሮች ተቋርጦ የነበረውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ከመለሰሳቸው በተጨማሪ በአሥመራና በአዲስ አበባ መሃከል የሚያደርጉትን የዓየየር በረራ እና የወደቦች ግንባታ እና አገልግሎትም መልሰው ለመጀመር ተስማምተዋል።

ኤርትራ በኢትዮጵያ የነበራትን ኤምባሲ ከፈተች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:17 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG