አዲስ አበባ —
ከጥቂት ወራት በፊት ዶ/ር አብይ አሕመድ በጠ/ሚኒስትርነት ተሹመው የመጀመሪያውን የመሪነት ንግግራቸውን ሲያደርጉ፣ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ልብ ማርከዋል ቀልብም ስበዋል። ይህ ስሜት እስከዛሬም ይበልጥ እየጋለ እንደሚሄድም ብዙዎች ይናገራሉ።
ሰኔ16 ቀን የአዲስ አበባና አካባቢው ሕዝብ የጠ/ሚኒስትር አብይን አመራር በመደገፍ በመስቀል አደባባይ ሰልፍ ከወጣ በኋላ በሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተመሳሳይ ሰልፎች ተደግመዋል። ከእነዚህ አንዱ በአማራው ክልል በባህር ዳር ከተማ የተካሄደው መሆኑ ይታወሳል። ይህ የድጋፍ ሰልፍ በዓላማው የተለየ ነው ባይባልም ተጨማሪ ይዘት እንዳለው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
ሰልፉና በሰልፉ ላይ የተደረጉ ንግግሮች በአማራ ብሄርተኝነትና በኢትዮጵያ ብሄርተኝነት አንድነትና ልዩነት በጠንካራ መልኩ ያንፀባረቀ ነው ተብሏል።
መለስካቸው አምሃ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር የሆኑትን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን አነጋግሯል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ