በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን መነሲቡ ወረዳ መንዲ ከተማ ረቡዕ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም በሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች ተፈፀመ በተባለ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መጎዳታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
በዳውድ ኢብሳ ከሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች ጋር የሚወያይ የኢትዮጵያ መንግሥት የልዑካን ቡድን አሥመራ መሄዱ፣ በዚያውም ከኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መገናኘቱ ታወቀ።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ እና ምዕራብ ወለጋ ውስጥ በመንግስት ታጣቂዎች የሚፈፀም ግድያ መቀጠሉን እንዲሁም በአጄ ከተማ በነዋሪዎችና በታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከሕዝቡም ከታጣቂዎችም ሕይወት መጥፋቱን ነዋሪዎች ገለጹ።
ልጃቸው አስከሬን ላይ እንደተደበደቡ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት እናት በተባለው ቤት እንደማይገኙ የመንግሥት ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሐምድ ሰኢድ መናገራቸው ይታወሳል። የዞን ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ደግሞ ሟቹም ኤፍሬምም እናቱም ወ/ሮ ታደሉ የከተማው ነዋሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሉም የተባለው በመረጃ ክፍተት መሆኑን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።
በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ ትናንት ማክሰኞ ማምሻው ላይ ከመንግሥት ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። የአንደኛው ወጣት ወላጅ እናት እኔንም የልጄ አስከሬን ላይ ጥለው ደበደቡኝ ብለዋል።
በምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ ትናንት ሰኞ ማታ ሁለት ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ሓይሎች መገደላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች እና የሆስፒታል ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲካሄድ የነበረው ተቃውሞ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በድጋሚ ማገርሸቱንና የሰባትና የ13 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሕፃናትን ጨምሮ በርካቶች እየተገደሉ መሆኑን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። “ወጥቼ ስመለስ የዐሥራ ሦስት ዓመት ልጄ አስክሬን እቤት ጠበቀኝ” ያሉ የአወዳይ ከተማ ነዋሪም ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) 26ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ተቃውሞ ገጠመው፡፡
በቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ ኑኑ ከተማዉ
በሁለቱም አካባቢዎች ማለትም በዳሮ ለቡ እና በዶሎ ማና በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የቀረቡ መፈክሮች፥ በመንግሥት ታጣቂዎች ይፈጸማሉ የተባሉ ድብደባዎች፥ እሥራትና ግድያ እንዲቆሙ ተጠይቆባቸዋል።
የኦሮሚያ ተቃውሞ ዛሬም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ መዋሉ ተነግሯል። አንዳንድ ባለሥልጣናት ግን የቆሰለም ሆነ የሞተም የለም ብለዋል።
ኦሮምያ ውስጥ በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ አካባቢዎች ሰሞኑን የታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዛሬም ቀጥሎ በተለይ በምሥራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።
ምዕራብ አርሲ ውስጥም ከከትናንት በስተያ አንስቶ ግጭቶች መኖራቸው ተሰምቷል።
በጉጂ ዞን በጎሮ ዶላ ወረዳ ሰሬንሳርና በምሥራቅ ሃረርጌ ዶባ ወረዳ በምሥችፍራ ከተሞች በዛሬው ዕለት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ተዘገበ።
የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረቦች ጃለኔ ገመዳ፣ ቱጁቤ ኩሳና ነሞ ዳንዲ ወደ ተለያዩ ከተሞች ደውለው ያጠናቀሯቸው ዘገባዎች አሉ። ሰሎሞን ክፍሌ ያጠናቀራቸው ዝርዝሮች።
“ካራ በተባለ ሥፍራ ነው፤ ዛሬ ጠዋት አራት ሰዓት ላይ ፖሊስ ተኩሶ የገደለው። በቀደመው ሰልፍ ላይ በመሳተፉ ነው፤ የተገደለው።” አንድ የሚኤሶ ከተማ ነዋሪ። “በመጀመሪያ ልዩ ፖሊስ ኃይል የሚባል በወረዳችንም ሆነ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የለም። ይህ ፕሮፖጋንዳና የሃሰት ወሬ ነው። በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ሥርዓት መሠረት ሰው በሰላም የመኖር መብት አለው።” አቶ መሃመድ ጀማል የሚኤሶ ወረዳ ምክትል ሊቀ መንበር።
ከአምቦ ከተማ ባለፈው ሃምሌ ወር ታስሮ በአዲስ አበባ እስር ቤት ሳለ ታሞ ሆስፒታል ህይወቱ እንዳለፈ የተገለጸው ተማሪ አብደታ ኦላንሳ ቀብር ዛሬ በአምቦ ከተማ ተፈጽሟል። የጸጥታ ሃይሎች ቀብር ሥነ ስርዓቱን ለማስተጓጎል ድብደባና እስር ፈጽመዋል። ትናንት አስከሬኑን ለመቀበል ተኩሰው የገደሉትም አለ ብለዋል።