ዋሽንግተን —
ተቃውሞው በምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ በምዕራብ አርሲና በምዕራብ ሸዋም እንዳለ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በምስራቅ ሐረርጌ አወዳይ ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ የገለጹት አቶ መሐመድ አብዱራህማን “የዐስራ ሦስት ዓመት ልጄ ተገሎብኛል፤ ቀብሩ ላይ መገኘትም አልቻልኩም” ይላሉ።
በምስራቅ ሐረርጌ የሰላምና መረጋጋት ኃላፊ ኢንስፔክተር ግርማ ገላን በበኩላቸው ሞቱ ስለተባሉት ሰዎች የተጣራ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው ሰልፉን በተመለከተ የመንግስትን ንብረት ለማውደም የተነሱ የሽብር መልዕክተኞች ነበሩ ሁኔታውን ተቆጣጥረነዋል ብለዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።