በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተቃዉሞ ያካሄዱ ተማሪዎች የጸጥታ ሃይሎች ደበደቡን ይላሉ


በአዳማ ዩኒቨርሲቲ
በአዳማ ዩኒቨርሲቲ

በቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ ኑኑ ከተማዉ

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ከተማ በሚገኘዉ የአዳማ ዩኒቬርሲቲ ትላንት ማታ የተማሪዎችተቃዉሞ መካሄዱን የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የኦሮሚኛ ቋንቋ ባልደረቦችን ያነጋገሩ ተማሪዎች ገልጸዋል።

ተማሪዎች በዩኒቬርሲቲዉ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ተቃዉሞ ሲያሰሙ የፖሊስና የመከላከያሰራዊት አባላት ደርሰዉ ድብደባ እንደፈጸሙባቸዉ ተናግረዋል።

የዩኒቬርሲቲዉ ፕሬዚደንት ሰለሰልፉና ደረሰ ሰለተባለዉ ድብደባ ተጠይቀዉ ሪፓርቱ እንደረሳቸዉ የበለጠ መግለጽ እንደይችሉግን ዘገባዉን ላጠናቀረችዉ የአፋን ኦሮሞ ስርጭት ክፍል ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ገልጸዋል።

በቄለምወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ ኑኑ ከተማዉ ባለፉት አራት ወራት እየተካሄደ ያለዉን ሰልፍ አደራጅታችሁዋል በመባል የአካባቢዉ ጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዉን እያሰሩ መሆኑ ለባልደረባችን ቱጁቤ ኩሳ ገልጸዋል፥ የክልሉ መንግስት ግን አስተባብሏል።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ዝርዝሩን ያድምጡ።

በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተቃዉሞ ያካሄዱ ተማሪዎች የጸጥታ ሃይሎች ደበደቡን ይላሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG