በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሟቹም ኤፍሬም እናቱም ወ/ሮ ታደሉ የከተማችን ነዋሪዎች ናቸው” የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ


ደምቢዶሎ ከተማ
ደምቢዶሎ ከተማ

ልጃቸው አስከሬን ላይ እንደተደበደቡ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት እናት በተባለው ቤት እንደማይገኙ የመንግሥት ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሐምድ ሰኢድ መናገራቸው ይታወሳል። የዞን ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ደግሞ ሟቹም ኤፍሬምም እናቱም ወ/ሮ ታደሉ የከተማው ነዋሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሉም የተባለው በመረጃ ክፍተት መሆኑን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

ማክሰኞ መስከረም 6 ቀን 2009 ዓ.ም ማምሻውን በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ ከመንግሥት ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው እንዳለፈ ከተነገረው አንዱ ወጣት ወላጅ እናት ልጃቸው አስከሬን ላይ እንደተደበደቡ መናገራቸው ይታወሳል።

የመንግሥት ኮሙዩኔኬሽን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሰኢድ ሆነ ተብለው የሚሰራጩ የተሳሳቱ የስብዓዊ መብት ጥሰት መረጃዎች እንዳሉ ጠቅሰው እንዲህ የሚባሉ ሴት በተጠቀሰው አድራሻ የሉም በሚል አስተባበለው ነበር።

በሌላ በኩል የቄለም ወለጋ ዞን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዘመነ ጥጋቡ ሟቾቹ ወጣት ኃይሉ ኤፍሬምና ወጣት ኢብሳ ሩንዴ እንዲሁም የኤፍሬም እናት ወ/ሮ ታደሉ ተማም የከተማችን ነዋሪዎች ናቸው።

ሆኖም በፌደራል ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የፌስ ቡክ ገጽ ላይ "እንዲህ የሚባሉ ግለሰቦች የአካባቢ ነዋሪዎች አይደሉም" በሚል በመስከረም 12 በአሜሪካ ድምጽ ላይ የተገለጸው በመረጃ ክፍተት መሆኑን አስፍሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ።

“ሟቹም ኤፍሬም እናቱም ወ/ሮ ታደሉ የከተማችን ነዋሪዎች ናቸው” የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00

XS
SM
MD
LG