በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኦነግ አመራሮች ጋር ለመወያየት አሥመራ የተጓዘው ልዑካን ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ተገናኘ

በዳውድ ኢብሳ ከሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች ጋር የሚወያይ የኢትዮጵያ መንግሥት የልዑካን ቡድን አሥመራ መሄዱ፣ በዚያውም ከኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መገናኘቱ ታወቀ።

በዳውድ ኢብሳ ከሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች ጋር የሚወያይ የኢትዮጵያ መንግሥት የልዑካን ቡድን አሥመራ መሄዱ፣ በዚያውም ከኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መገናኘቱ ታወቀ።

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና አቶ ለማ መገርሳ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በነበራቸው ቆይታም በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተነግሯል። እንዲሁም በቅርቡ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተፈረመው የሰላምና የወዳጅነት ሥምምነት ተፈፃሚ የሚደረግበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል። የልዑካኑ ቡድን አባላት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳና የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ሲሆኑ፣ ከኦነግ አመራሮች ጋር እንደተወያዩም ተገልጧል።

የኦነግ አመራሮች ከኢትዮጵያ መንግሥት ልዑካን ጋር በምን ጉዳይ ተወያይተው ምን ውሳኔ ላይ እንደደረሱ፣ የአፋን ኦሮሞ ክፍል ባልደረባችን ቱጁቤ ኩሳ አጠናቅራለች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ከኦነግ አመራሮች ጋር ለመወያየት አሥመራ የተጓዘው ልዑካን ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ተገናኘ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:14 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG