ኦሮሚያ ክልል ሦስት ወራት የተጠጋው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዛሬም በአንዳንድ አካባቢዎች ቀጥሏል።
የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረቦች ጃለኔ ገመዳና ነሞ ዳንዲ ወደ ተለያዩ ከተሞች ደውለው ያጠናቀሯቸው ዘገባዎች አሉ።
በዩናይትድ ስቴትስ የሚኔሶታ ሁለት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላትም በጋራ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ በሁኔታው አሳሳቢነት ላይ የፃፉት ደብዳቤ አለ፤ ሰሎሞን ክፍሌ ሁሉንም አካትቶ እንደሚከተለው ያቀርበዋል። የትናንትና ዘገባውን ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን ፋይል በመጫን ያዳምጡ።
በተጨማሪም ዛሬ በቦረና ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ ውስጥ የፀጥታ ኃይሎች አንድ ሰላማዊ ሰው ላይ ተኩሰው ካቆሰሉ በሁዋላ፥ ተቃውሞ ተነስቷል። በጀልዱም የተቃውሞ ሰልፎች መካሄዳቸው ተዘግቧል። በትላንትናው እለት በምሥራቅ ወለጋ ዞን ኑኑ ቁምባ ወረዳና በጉጂ ዞን በኦኮቴ ከተማ ስለደረሱ ግጭቶች ባቀረብናቸው ዘገባዎች ላይም የባለሥልጣናት ምላሾችን ይዘናል።
የአፋን ኦሮሞ አገልግሎት ባልደረቦች ጃለኔ ገመዳ፥ ቱጁቤ ኩሳ እና ነሞ ዳንዲ ያጠናቀሯቸው ዘገባዎች አሉ። ሰሎሞን ክፍሌ እንደሚከተለው አቅርቦታል። የዛሬውን ዘገባ ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።