አሜሪካ ኢትዮጲያ ውስጥ ድርቅ ላጠቃቸውና ለስደተኞች መርጃ የሚውል $97 ሚልዮን እርዳታ ሰጠች።
የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ወገኖች በጁባና በሌሎችም ዋና ዋና ከተሞች በሚሰፍረው ኃይል ቁጥር ላይ ተስማሙ።
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ስለ ባለፉት አራት ዓመታት ያከናወናቸው ተግባራት ውጤቶችን የሚያሳይ አንድ መቶ ዐስር ገጽ የሚሆን ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጽያ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወንዲራድ ማንደፍሮ የምግብ እጥረት ላጋጠማቸዉ ኢትዮጵያዉያን መንግስት አብዛኛዉ እርዳታ እየቀረበ ነው አሉ። በዘንድሮው ድርቅ ምክንያት የምርት መጠን እንደማይቀንስም ተናገሩ።
በደቡብ ሱዳን የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና የጦር ወንጀሎችን የሚዘረዝረው ሪፖርት መውጣቱን የተቃዋሚው ቡድን እንደሚቀበለው አስታወቀ። መንግሥት እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።
በትጥቅ ትግል መንግሥት ለመቀየር እየሠሩ ያሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ውጤት እንደማያመጡ እርግጠኞች ነን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።
የሲቪክ ማህበራትና ነፃ ሚዲያ ሚና ወሳኝ መሆናቸውን የገለጹት የስዊዘርላንድ ፕሬዘዳንት ናቸው።
ኢትዮጵያ በኤነርጂ ዘርፍ ያለዉን ዓለምአቀፍ ልምድ እንድትቀስም እድል ይፈጥራል ሲሉ አንድ የዉሃ መስኖ ኤሌክትሪክ ሚኒስትር የስራ ሃላፊ ተናግረዋል።
የደቡብ ሱዳን መንግስት እና ተቃዋሚዎች በጦር ውህደት ላይ እስካሁን እልተስማሙም። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ስብሰባም ያለውጤት ቀጥሏል።
የቀድሞ የቦትስዋና ፕሬዚደንት ፌስቱስ ሞጋ (Festus Mogea) የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት መተግበሩን የሚከታተለዉን ኮሚሽን ለመምራት በሊቀመንበርነት መሾማቸዉ እንዳስደሰታት አሜሪካ አስታወቀች።
ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚቋቋመው የሽግግር መንግሥት የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትና የዶ/ር ሪያክ ማቻር ጦር የሚዋኻዱበትን ሁኔታ የሚያቅድ ስብሰባ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተከፍቷል፡፡
በኤል ልኒኖ ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ እርዳታ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ወደ 8 ሚልዮን ደርሷል።
ከኢትዮጵያው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ያካሄዱት ውይይት መልካም እርምጃ መሆኑን ተሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ።
ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለው ረሃብ የገዥው ፓርቲን ፖሊሲ ውድቀት ያሳያል ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሰ፡፡
ለመጪዎቹ አምሥት ዓመታት በጠቅላይ ሚንስትርነት እንዲቀጥሉ የተሰየሙት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አዲሱን ካቢኔያቸውን ዛሬ ይፋ አድርገዋል።
የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው የምስረታ ጉባኤ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧቸዋል፡፡
“የአገራችን ኢኮኖሚ ፈጣንነቱንና ፍትሃዊነቱን በማስጠበቅ ባሳለፍነው ዓመትም ባለ ሁለት አሃዝ ሆኖ ተመስግቧል።” የኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ።
ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ መቶ በመቶ የሚቆጣጠረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪዎቹን ይመርጣል
ዴሞክራሲ በሌለበትና ሰብዓዊ መብቶች ባልተከበሩበት ሁኔታ መልካም አስተዳደር ሊረጋገጥ አይችልም ሲሉ የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ