በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳናዊያን ስምምነታቸውን ለመተግበር ስብሰባ ተቀመጡ


ማይክል ማኩየይ ሉየዝ እና ታባን ዴንግ ጋይ
ማይክል ማኩየይ ሉየዝ እና ታባን ዴንግ ጋይ

ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚቋቋመው የሽግግር መንግሥት የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትና የዶ/ር ሪያክ ማቻር ጦር የሚዋኻዱበትን ሁኔታ የሚያቅድ ስብሰባ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተከፍቷል፡፡

ደቡብ ሱዳናዊያን ስምምነታቸውን ለመተግበር ስብሰባ ተቀመጡ /ርዝመት፡-3ደ31ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:31 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚቋቋመው የሽግግር መንግሥት የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትና የዶ/ር ሪያክ ማቻር ጦር የሚዋኻዱበትን ሁኔታ የሚያቅድ ስብሰባ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተከፍቷል፡፡

በፀጥታ መዋቅሮች ላይ መስማማት ለሽግግር መንግሥቱ መሣካት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን /ኢጋድ/ ዋነኛ አደራዳሪ አምባሣደር ስዩም መስፍን ተናግረዋል፡፡

ወገኖቹ ስብሰባ የተቀመጡት በመንግሥቱ ተጠባባቂ ዋነኛ ተደራዳሪና የማስታወቂያ ሚኒስትር ማይክል ማኩየይ ሉየዝ እና በተቃዋሚዎቹ ዋነኛ ተደራዳሪ ታባን ዴንግ ጋይ የቡድኖች መሪነት ነው፡፡

ስብሰባው እየተካሄደ ያለው ባለፈው ነኀሴ መጨረሻ ላይ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ለመተግበር እንጂ ድርድር እንደገና ለመክፈት አለመሆኑን የኢጋዱ ዋና አደራዳሪ አምባሣደር ስዩም አሳስበዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG