በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጽያ መንግስት የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው እርዳታ እያቀረበ ነዉ


የኢትዮጽያ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወንዲራድ ማንደፍሮ የምግብ እጥረት ላጋጠማቸዉ ኢትዮጵያዉያን መንግስት አብዛኛዉ እርዳታ እየቀረበ ነው አሉ። በዘንድሮው ድርቅ ምክንያት የምርት መጠን እንደማይቀንስም ተናገሩ።

በተለያዩ የኢትዮጽያ አካባቢዎች በተከሰተዉ ድርቅ ምክንያት የአገሪቱ የዚህ ዓመት አጠቃላይ ምርት መጠን እንደማይቀንስ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በተሻሉ ቦታዎች በሰራነዉ ስራ ምክንያት የበለጠ እንጂ ያነሰ የምርት መጠን አንጠብቅም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ ወንዲራድ ማንደፍሮ የምግብ እጥረት ላጋጠማቸዉ ኢትዮጵያዉያን አብዛኛዉ እርዳታ እየቀረበ ያለዉም በራሱ በመንግስት አቅም ነዉ ብለዋል።

በአሁኑ ድርቅ የምግብ እርዳታ የሚፈልገዉ ሕዝብ በደርግና በንጉሱ ዘመን ከነበሩ ይበልጣል በሚል ለተነሳዉ ጥያቄም ቁጥሩ በመቶኛ መሰላት እንዳለበት አሳስበዋል።

ዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬዉ ዛሬ ሚኒስትሩ የሰጡትን መግለጫ ተከታትሎ ቀጣዩን ዘግቧል። ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

የኢትዮጽያ መንግስት የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው እርዳታ እያቀረበ ነዉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:02 0:00

XS
SM
MD
LG