አዲስ አበባ —
ለመጪዎቹ አምሥት ዓመታት በጠቅላይ ሚንስትርነት እንዲቀጥሉ የተሰየሙት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አዲሱን ካቢኔያቸውን ዛሬ ይፋ አድርገዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ አቶ ደመቀ መኮንንና በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት ማዕረግ የተለያዩ ዘርፎችን የሚያስተዳድሩት ዶ/ር ደብረ-ጽዮን ገብረሚካኤልና ወ/ሮ አስቴር ማሞ በያዙት ኃላፊነት ቀጥለዋል። ከተሾሙት ሃያ ስድስት የካቢኔ ሚንስትሮች አብዛኞቹም በያዙት ኃላፊነት የሚቀጥሉ ናቸው።
በሌሎች ተሿሚዎች ከተተኩት ሚንስትሮች መካከል ረዘም ላሉ ዓመታት በገንዘብና የምጣኔ ሃብት ልማት ሚንስትርነት ያገለገሉት አቶ ሱፍያን አህመድ ይገኙበታል።
እስክንድር ፍሬው አቀናብሮ የላከውን ዘገባ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምቱ።
እስከንድር የተቃዋሚዎችን አስተያየትንም ሰብስቧል። ይህን ከታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
የፎቶ መድበሎቻችንንም ይመልከቱ።