በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተቃዋሚዎች መንግሥት በኃይል ለመለወጥ አይችሉም አሉ


ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

በትጥቅ ትግል መንግሥት ለመቀየር እየሠሩ ያሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ውጤት እንደማያመጡ እርግጠኞች ነን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።

የዋህ ዳያስፖራዎች የሚሰጡትን ገንዘብ ለመሰብሰብና ለማካበት ካልሆነ በቀር ትርጉም ያለው ነገር እንዳልሆነ የሚታወቅ ነው ብለዋል። በእኛ እምነት ይሄን ነገር ትተው እየበለጸገችና እያደገች ያለች ሀገራቸው የሃሳብ ልዩነት ካላቸውም፥ በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ በሚያቀርቡበት ደረጃ ላይ የደረሰች በመሆኗ፥ ወደ ሰላማዊ መሥመር ቢመጡ ይሻላቸዋል ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየት ከመንግሥታቸው የምህረት ውሳኔ ጋር ተገጣጥሟል። እስክንድር ፍሬው የላከውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተቃዋሚዎች መንግሥት በኃይል ለመለወጥ አይችሉም አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:11 0:00

XS
SM
MD
LG