አዲስ አበባ —
ባለፉት አራት ዓመታት ባከናወናቸው ተግባራት ውጤቶች መገኘታቸውን፤ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ባለ አንድ መቶ ዐስር ገጽ ሪፖርት አስታውቋል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሊድ ቦምባ ለአሜሪካ ድምጽ እንዳብራሩት በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት የተሠሩ ሥራዎች አርሶ አደሩን በቀጥታ ተተቃሚ ያደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡ከተቋቋመ አራት ዓመታትን ያስቆጠረው ኤጀንሲው ምን ሲሠራ ቆየ?
የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬው ለአቶ ካሊድ ቦምባ በመጀመሪያ ያቀረበው ጥያቄ ነው። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።