በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተሳተፉበት የጎንደር የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ የሞከሩት በህወሓት የተላኩ ግለሰቦች ናቸው፤ ሲሉ አንድ ከፍተኛ የአማራ ክልል የፀጥታ ባለሥልጣን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የነአቶ በረከት ስምዖንን የመከላከያ ምስክሮች ለመስማት ለታህሳስ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
በየዩኒቨርስቲዎች እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶችን መንግሥት ለማስቆም አፉጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ፡፡
“ይህን የፈጸሙ አካላት ለፍርድ ይቀርባሉ። የምንደራደረው ጉዳይ አይደለም። ዩኒቨርሲቲዎቻችን የምርምር ተቋማት እና የኢትዮጵያዊነት መለጫ ሞዴሎች ናቸው። ሰላም እንዲሆን እንፈልጋለን።የድንጋይ መወራወሪያ የጸብ ማጫሪያ የሴራ ማሰሪያ እንዲሆኑ አንፈልግም። የምርምር ተቋም ብቻ እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው።” የአማራ ክልል ፖሊስ ኮምሽነር አበረ አዳሙ።
በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ይዘው የቀረቡ ምሁራንና ግለሰቦች የሚያሰራቸው አካል እንዳላገኙ ተናገሩ።
ዛሬ ማምሻውን ከእስር የተለቀቁት፤የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ኃላፊ የነበሩት ብሪጋዲየር ጄነራል ተፈራ ፣ የክልሉ ሕዝብ ደህንነትና የሰላም ግንባታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል አለበል አማረና የአማራ ክልል ሚሊሽያ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል በአምላኩ አባይ መሆናቸውን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ኢዮብ ጌታቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በማይወጡ ሚዲያዎች ላይ መንግሥት ዕርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ አንዳንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ።
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮምሽን የኢንፎርሜሽን እና ሚዲያ ልማት ዋና መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮምሺነር ሰይድ አህመድ ባለፈው ዓርብ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተውቋል።
በባህር ዳር ከተማ አልፎ አልፎ ምሽት ላይ የሚሰማው የተኩስ ድምፅ ምንነት ግራ እንዳጋባቸው ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።
ላለፍት 7 ቀናት ሲያካሂዱት የነበረውን ፀሎተ ምህላ ያጠናቀቁት በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ምዕመናን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ይፈፀማሉ ያሏቸው ጥቃቶች እንዲቆሙ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በየክልላችሁ ተዋልደውና ተጋምደው የሚኖረውን የአማራ ህዝብ፣ በቆየው ኢትዮጵያዊው የመፈቃቀር መንፈስ አቅፋችሁ ኑሩ ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲሱን ዓመት ምክንያት በአማራ ክልል ከ4ሺ በላይ ታራሚዎች እንዲለቀቁ ተወስኗል።
የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና 645 በማምጣት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የተባለውን ውጤት ያስመዘገበው ብሩክ ዘውዱ እና ወላጅ እናቱ ኤልሳቤት ጥላሁን ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በነብርጋዴል ጀነራል ተፈራ ማሞ የምርመራ መዝገብ ከሁለት ሳምንት በፊት የባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ውድቅ ያደረገውን ተጨማሪ የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ የባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት አፀና።
በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ጋር የተደረገ ውይይት፡፡
በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/አብን/ የብሔራዊ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ከሆኑት አቶ ተሰማ ካሳሁን ጋር የተደረገ ውይይት፡፡
በአማራ ክልል ያለፈው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ ወቅት “የቁጥጥር መላላት ነበር” የሚል ለክልሉ የትምህርት ቢሮም ለሃገር አቀፉ የፈተናዎችና ምዘና ኤጀንሲም የቀረበ ቅሬታ እንደሌለ የክልሉ የትምህር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ ገልፀዋል።
በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች የሚገኙ ትውልደ - ኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው ብባህርዳር ከተማ ከኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
"አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ታፍሰው ታሰሩብን" ሲል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ አቤቱታ አሰምቷል።
ባህር ዳር ላይ በተካሄደ የአማራ እና የሶማሌ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ተገኝተው ተናግረዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ