በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእምቦጭ አርምን ለማጥፋት የተሰማሩ ምሁራን ቅሬታ አሰሙ


ፎቶ ፋይል፦እምቦጭ
ፎቶ ፋይል፦እምቦጭ

በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ይዘው የቀረቡ ምሁራንና ግለሰቦች የሚያሰራቸው አካል እንዳላገኙ ተናገሩ።

በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት ሚሊዮን ብሮች ወጥቶባቸው የተገዙ ማሽኖችም ያለ ሥራ እንደቆሙ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ቅሬታ የቀረበበት የክልሉ የአካባቢ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለሥልጣን መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

በቅርቡ የጣናን ጉዳይ እንዲከታተል የተቋቋመው የጣና ሀይቅና ሌሎች ውሃማ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ በበኩሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተቀናጀና ቅደም ተከተላዊ በሆነ መንገድ የእንቦጭ አረምን ከጣና ሀይቅ ላይ አስወግዳለሁ እያለ ነው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የእምቦጭ አርምን ለማጥፋት የተሰማሩ ምሁራን ቅሬታ አሰሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:14 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG