በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነአቶ በረከት ስምዖንን የመከላከያ ምስክሮች ለመስማት ተቀጠረ


የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የነአቶ በረከት ስምዖንን የመከላከያ ምስክሮች ለመስማት ለታህሳስ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የአቶ በረከት ሰምዖንንና የአቶ ታደሰ ካሳን የመከላከያ ምስክሮች ለመስማት የተሰየመ ቢሆንም 1ኛ ና የ2ኛ ተከሳሽ የሰነድና የሰው ምስክሮች ባለመቅረባቸው ለሌላ ጊዜ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የነአቶ በረከት ጠበቃ “በተለይ አስፈላጊ የሆኑ የመከላከያ ሰነዶች ለዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ መድረስ ስላልቻሉ ከቀጣዩ ቀጠሮ ቀን በፊት እንድናቀርብ ይፈቀድልን” ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡

አቃቤ ህግ የተሰጠው ምክንያት ተቀባይነት የለውም በማለት ቅሬታ ቢያቀርብም በአጭር ጊዜ ሰነዶቹን የሚያቀርቡ ከሆነ እንደማይቃወም ተናግሯል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የነአቶ በረከት ስምዖንን የመከላከያ ምስክሮች ለመስማት ተቀጠረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:58 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG