በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች


የኢትዮጵያ መንግሥት የታገቱ የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በተመለከተ በቂ ትኩረት አልሠጠም ያሉ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተማዎች ዛሬ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል።

መንግሥት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ተገቢውን እርምጃ አልወሰደም ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተም ግልፅ መረጃ እየሠጠ አይደለም በማለትም ሰልፈኞቹ ገልፀዋል።

በሠልፉ ላይ ንግግር ለማድረግ በባህር ዳር እስታድዬም የተገኙ ከፍተኛ የአማራ ክልል ባለሥልጣናት በገጠማቸው ከፍተኛ ተቃውሞ የመጡበትን ጉዳይ ሳያከናውኑ ተመልሰዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ

የጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት የታጋች ቤተሠቦችን መጥራቱን የገለፁ አንዳንድ የቤተሰብ አባላት ወደ ዛው እያመሩ መሆናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በሌላም በኩል ከወራት በፊት በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተደረገውን እገታ የሚያወግዝ ሰልፍ ዛሬ በሰሜን ወሎና ሰሜን ሸዋ ዞኖች በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተካሂዷል፡፡

በሰልፉ ላይ እናቶችን ጨምሮ ቁጥራቸው በርካታ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ሰልፈኞቹ መንግሥት የታገቱ ተማሪዎችን ለማስለቀቅ ያደረገው ጥረትና ትኩረት አናሳ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:49 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG