በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከትላንት በስትያ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተማሪዎች ተገደሉ


Woldia University
Woldia University

“ይህን የፈጸሙ አካላት ለፍርድ ይቀርባሉ። የምንደራደረው ጉዳይ አይደለም። ዩኒቨርሲቲዎቻችን የምርምር ተቋማት እና የኢትዮጵያዊነት መለጫ ሞዴሎች ናቸው። ሰላም እንዲሆን እንፈልጋለን።የድንጋይ መወራወሪያ የጸብ ማጫሪያ የሴራ ማሰሪያ እንዲሆኑ አንፈልግም። የምርምር ተቋም ብቻ እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው።” የአማራ ክልል ፖሊስ ኮምሽነር አበረ አዳሙ።

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከትላንት በስትያ ምሽት በተማሪዎች መሃከል በተቀሰቀሰ ግጭት ሁለት ተማሪዎች መገደላቸውን ሌሎች ቁጥራቸው አሥር የሚደርስ ተማሪዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የዩኒቨውርሲቲው ተማሪዎችና ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የመንስኤው ምንነት ለጊዜው ያለመታወቁን የዩኒቨርሲቲው ባለሥልጣናት ይናገራሉ። የክልሉ ፓሊስ በበኩሉ የወንጀሉን መንስኤና የገዳዮች ማንነት በማጣራት ላይ መሆኑን፤ የወንጀሉ ፈጻሚዎች እንደታወቁም ሕግ ፊት እንደሚቀርቡ አስታውቋል።

በሌላ ተያያዥ ዜና የሁለት ተማሪዎች ሕይወት የጠፋበትን ድንገት “በሰላማዊ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመ ድብደባ” ያሉት የኦሮምያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኦቢኤ’ን ቴሌቭዥን ላይ በተነበበው መግለጫቸው “አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአቋራጭ ስልጣን ፍለጋ ሕዝቡን እያስጨነቁ ይገኛሉ። ባሁኑም ወቅት ሁኔታዎችን እየመረጡ ግጭት በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ።” ሲሉ ከሰዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹን ማንነት ግን በስም አልገለጹም።

ለዝርዝሩ መስፍን አራጌ ከደሴ አስቴር ምስጋናው ከባሕር ዳር ያጠናቀሯቸው ዘገባዎች ይዳምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG