“እኔ እንደሚመስለኝ ሙዚቃ ምናልባት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው አንድ ምትሃታዊ ጥበብ ነው የሚመስለኝ።” ሄኖክ ተመስገን - ሙዚቀኛ። “... መንፈስ የሚያጥብ ነው ሙዚቃ። ... እርግጥ እንደ ሙዚቃው ዓይነት ነው።.. ለምሳሌ ትዝ ይለኛል በ1970ዎቹ የአስቴርን ሙዚቃ በምንሰማበት ጊዜ ፍቅር ያልያዘው ሰው እንኳን ፍቅር እንደ ያዘው እንዲሰማው ያደርጋል የአስቴር ሙዚቃ። ...” ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ - የአንጎል ሃኪም።
“.. ሁሌም የምታሰበው ያንን ሥራ ሰርቼ ሕዝብ ጋ ደርሶ እያልክ ነው። .. ከተሠራ ለዕይታ ከበቃም በላ ቢሆን ‘መሻሻል አለበት’ በሚል እኔ አልረካም። .. ሰው ተመልክቶ ሲደሰት ሳይ ደግሞ ለራሴም ይገርመኛል።” መራሔ ጥበብ ታደሰ ወርቁ።
“አንድ ዕድል ነው ያለን! በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይገባ መከላከል ካልቻልን፤ አንዴ ይሄ ሕመም ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባ የጤና ተቋማቱ አቅቅም የተሟላ ባለመሆኑ - ‘ከገባ በኋላ እንሰራለን’ የሚል ሃሳብ እዚህ ላይ የሚሰራ አይደለም።” ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ። “ይሄ በሽታ እየጨመረ መሄዱና የአንዳንድ አገሮች ደግሞ ያን የመቋቋም አቅም ጠንካራ አለመሆን በተለይ ለእንደ እኛ ዓይነት አገሮች አሳሳቢ ነው።” ዶ/ር ሊያ ታደሰ።
“..የመንግስት ደጋፊ ወይም የተቃዋሚ ደጋፊ .. የዚህ ሃይማኖት አለያም የዚያ ሃይማኖት ደጋፊ ልንሆን አንችልም። ለሃገሬ አልቆረቆርም ማለት አይደለም .. ጋዜጠኝነት .. የእኛ ታማኝነት ግን ሃቅ ላይ ለተመረኮዘ ጋዜጠኝነት ነው።” ንጉሴ መንገሻ የአሜሪካ ድምጽ የአፍሪቃ ዋና ክፍል ዲሬክተር።
“አደንጋጭ ከሆኑት የኮሮናቫይረስ ይሄ ሶስተኛው ነው። በተፈጥሮው ከአእዋፋት ወደ ሰው የሚተላለፍ ቫይረስ አደገኛ የሚሆነው ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ ሲጀምር ነው። አሁን ከዚያ የደረሰ ይመስላል። አሳሳቢ ያደረገውም ያ ነው።” ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ክፍል ፕሮፌሰር።
“ኢትዮጵያን በሚመለከት በአንድ በኩል ብዙ ተሥፋ የሚሰጥ በሌላ በኩል ደግሞ ተሥፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ ባይም፤ ይሁንና የእኔ መንገድና የእኔ እምነት - ትኩረቴ ተሥፋ ሰጭ በሆኑ ነገሮች ላይ ብናተኩር እንሻገራለን በሚል ስለሆነ የምጽፈውም የምናገረውም ተሥፋ በሚሰጡ ነገሮች ላይ ነው።”ዶ/ር ጌብ ሃምዳ።
"የህይወት ፍልስፍና የምለው አንድ ነገር አለኝ። ከደቡብ አፍሪቃውያን አባባል ነው። በጣ ስለምወደው እንደራሴ ነው የማየው። 'ኡቡንቱ' .. 'የኔ መኖር በአንተም ነው' እንደማለት። የአንዳችን ለሌላችን ስለመፈጠራችን በጣም እርግጠኛ ነኝ።” ዶ/ር ሰላም አክሊሉ።
ቆይታ ከ”አሥር ለጤና “ እና “ቀጥ ከልጅነት” ዘመቻዎች መሪ ዶ/ር ሰላም አክሊሉ ጋር Words of Wisdom: A New Year’s Perspective
“ቀኑ መልስ ይሁን!” የሚለው ዜማ ኤሊዛቤጥ ፓተርሰን የምትባል አንዲት የማውቃት በእጅጉ መንፈሳዊ የሆነች ሴት ናት መነሻዋ። የአምላክን አመላካችነት ከልቧ በመሻት በምታደርሰው የማለዳ ፀሎቷ እና ቀኑን በምትቀበልበት ዕምነቷ ትታወቃለች።..”
“አማርኛ ዘፈን መጫወት ስጀምር በማሕሙድ አህሙድ ‘ከአንች በቀር ሌላ’ እና ቴዎድሮስ ታደሰ ‘ግርማ ሞገስ’ ነበር የጀመርኩት።”ድምጻዊት ቤቲ ጂ።
"ከአርባ ዓመታት በፊት ከሆነው የተማርን አይመስለኝም። ተስፋ መቁረጤ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ግን አንድ እርምጃ ወደፊት ሄደን አራት ወደ ሁዋላ የምንል ይመስለኛል። ምን ዓይነት ሕዝብ ነን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።"ዶ/ር ሞገስ ገብረማሪያም። "ከዛ ትውልድ የምንማርው ከፍተኛ የአገር ፍቅር የነበረው ራሱን የሰጠ መሆኑን ነው። የትኛውም ቢሆን ታዲያ ምን ዓይነት የአንድ ወገን ዕውቀት ርዕዮተ ዓለም የሃገሪቷን ችግር በብቻው ሊፈታ ያለመቻሉን ነው።"አቶ ነዓምን ዘለቀ።
“..ኢትዮጵያን ሲያማት ያመናል የምንልበት ጊዜ ነውና .. ከምንግዜውም በላይ ጸሎት የሚያስፈለገን ጊዜ ነው እላለሁ ..”
በመቀሌው ጉባኤ እንድንሳተፍ ብንጋበዝም ላለመሳተፍ በመወሰናችን "አልተሳተፍንም" ይላሉ።
“እውነት ለራሱ ሲባል አይዘገብም ይባላል። ጋዜጠኛው እንደ ሃኪሙ የሚያደርገው ነገር፣ የሚሠራው ሥራ የሚወስነው ውሳኔ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ስላለ ያንን ተጽዕኖ እየተከተለ ነው መዘገብ ያለበት።” ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው። “...የዜናው አዘጋገብ ግጭቱን ይፈታል፣ ግጭቱን ይቀንሳል ወይንስ ባለበት ያቆየዋል የሚሉት ሁሉም ሊከተሰቱ የሚችሉ ውጤቶች በመሆናቸው ነው ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቀው።” ዶ/ር ቴዎድሮስ ወርቅአለማሁ ወርቅነህ።
“ሁላችንንም ተሸክማን የምታድር አገራችንን እንዳናጣት አንዱ አንዱ ላይ ነግሶ ለመታየት ከሚደረግ ሩጫ ተቆጥበን፤ ሁላችንም ዝቅ ብለን አገራችንን ከፍ ማድረግ የምንችልበት፤ የጋራ ታሪክ የምንጽፍበት፤ የጋራ ሃዘን ታሪካችንን ምዕራፎች የምንዘጋባቸው መንገዶች መጀመር አለብን።” የትነበርሽ ንጉሴ - የእርቀ ሰላም ኮምሽን ምክትል ሰብሳቢ።ኮምሽን ምክትል ሰብሳቢ።
"የአሜሪካ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ኃይሎች ትላንት ለሊት በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ቆራጥንነት የተመላና እጅግ አደገኛ ወታደራዊ ኦፕሬሽን አካሂደው ተልዕኳቸውን በድል አጠናቀዋል።” የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ።
“እንደ ራሳችሁ ሰው እንደተቀበላችሁኝ ‘አገሬ’ አድርጌ የተቀበልኩዋትን አገር ወክዬ ስቀርብ ታላቅ ኩራት ነው የተሰማኝ። .. ለአሕጉረ-አፍሪቃ የመጀመሪያ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ‘የባሕል መስክ’ ለመሰየም ስንበቃም የሰው ልጆች ምንጭ ከሆነችው አገር ታሪካችን እንደ መተሳሳር የሚቆጠር ነው።”
ተጨማሪ ይጫኑ